×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የቴሌኮመኒከሽን አዋጅ ቁጥር ፵፱/፲፱፻፹፱

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሦስተኛ ዓመት ቁጥር ፭ አዲስ አበባ - ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፷፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፵፱ ዓም የቴሌኮሙኒኬሽን አዋጅ . . . . . . . . . ገጽ ፪፻፻፬ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፫፱ ስለ ቴሌኮሙኒኬሽን የወጣ አዋጅ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለሀገሪቱ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ፣ | የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎትን ይበልጥ ቀልጣፋና አስተ ማማኝ ለማድረግ የቁጥጥር ተግባር የሚያከናውን አካል አገልግ ሎቱን ከሚሰጠው ድርጅት ለይቶ ማደራጀትና ቁጥጥሩ የሚካሄ ድበትን ሁኔታ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ! በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የቴሌኮሙኒኬሽን አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፱ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ ቴሌኮሙኒኬሽን ” ማለትድምጽ ' ምልክት ' ጽሑፍ ' ምስል ወይም ማናቸውም ዓይነት ሌላ መረጃ በኤሌክ ትሪክ ወይም በኤሌክትሮማግኔቲክ ኃይል አማካይነት ያንዱ ዋጋ 10 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ተሺ፩ ጽ ፪፻፸፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ኅዳር ፲፱ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta - No . 5 28 November 1996 - - Page 275 በስልክ ሽቦ ፡ በሬዲዮ : በኦፕቲካል ወይም በሌላ ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ስልት ማሠራጨት ፡ ማስተላለፍ ወይም መቀበል ሲሆን በማሠራጨቱ ፡ በማስተላለፉ ወይም በመቀበሉ ሂደት ድምጹ ፡ ምልክቱ : ጽሑፉ ሃረሉ ወይም መረጃውእንደገናመደራጀቱወይምበሌላ ፡ ክድለውጥ የተደረገበት መሆኑልዩነት አያመጣም ፤ የቴሌኮሙኒኬሽን መስመር ” ማለት ከቴሌኮሙኒኬሽን ሲስተም ጋር ለተያያዘ አገልግሎት የዋለ ወይም እንዲውል የታቀደ የስልክሽቦ ፡ ኬብል ' ታወር ማስት ፡ አንቴና ፡ ምሰሶ ወይምማናቸውም ሌላ ስትራክቸር ወይም መሣሪያ ነው ፤ ፫ . “ መሠረታዊ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ” ማለት _ የቴሌፎን | የቴሌግራም ወይም የቴሌክስ አገልግሎት _ ፩ “ የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያ ” ማለት ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የዋለ ወይም ሊውል የታቀደ ማንኛውም መሣሪያ . . ሲሆን , የመሣሪያውን ተገጣሚ አካል ይጨምራል ፤ . ፭ “ ቲቪ አርኦ ” ማለት በሳቴላይት አማካይነት የሚተ 3 ላለፍ የቴሌቪዥን ሥርጭት ለመቀበል ብቻ የሚያገ ለግል መሣሪያ ነው ፤ ፮ . “ የኮልባክ አገልግሎት ” ማለት የሀገር ውስጥ የቴሌኮሙ ኒኬሽን ድርጅት ሳያውቀው የሌላሀገርየቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የጥሪ ቶንን ለኢንተርናሽናል ግንኙነት መጠቀም ነው ፤ ፯ . “ ሚኒስቴር ” እና “ ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር እና ሚኒስትር ነው ፤ ፰ “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ክፍል ሁለት የቴሌኮሙኒኬሽን ኤጀንሲ - ፫ መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኤጀንሲ ( ከዚህ በኋላ “ ኤጀንሲው ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መሥሪያቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። ፪ : ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። - ፬ . ዋና መሥሪያ ቤት የኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደ | አስፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ . የኤጀንሲው ዓለም ጥራቱየተጠበቀ ' ቀልጣፋ ' አስተማማኝ ኤኮኖሚያዊ የሆነ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንዲስፋፉ ማድረግ ይሆናል ። - ፮ ሥልጣንና ተግባር ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለሀገሪቱ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ እድገት ተገቢውን አስተዋጽኦ ሊያበረክት በሚችል መልኩ መካሄዱን ያረጋግጣል ፤ ገጽ ያኔ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ኅዳር ፲ ) ቀን ፲፱፻፴፱ ዓ . ም . - Federal Negarit Gazeta - No . 5 28 November 1996 – Page 276 ፪• የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚሰጥበትን የቴክኒክ ደረጃና ሥርጭት ይወስናል ፡ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተወሰነለትን የጥራት ደረጃ ጠብቆ መሰጠቱን ይቆጣጠራል ፡ ፬• ለመሠረታዊ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚጠየ ቀውን ክፍያ ይቆጣጠራል ፡ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመስጠት ሥራ ላይ ለሚሰማሩ ፈቃድ ይሰጣል ፡ ይቆጣጠራል ፡ ፮ ከቴሌኮሙኒኬሽን ሲስተሙ ጋር ተገናኝተው ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉ የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያዎችን ዓይነት ይቆጣጠራል ፡ ለኢትዮጵያ የተመደበውን የሬዲዮ ፍሪኳንሲ ኣጠቃቀም ይፈቅዳል ፡ ይቆጣጠራል ፡ አግባብ ያላቸው ሕጎችና የመንግሥት መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፡ በሚኒስትሩ ሲወከል ቴሌኮሙኒኬ ሽንን በሚመለከቱ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዘንድ መንግሥትን ይወክላል ፡ ቴሌኮ ሙኒኬሽንን በሚመለከት ሀገሪቱ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ኣፈጻጸም ይከታተላል ፡ በቴሌኮሙኒኬሽን መስክ የሚሰጥ የቴክኒክ ትምህርት እንዲስፋፋ ከትምህርት ተቋሞች ጋር ይተባበራል ፡ የፈቃድ ክፍያዎችን ለሚኒስቴሩ አቅርቦ በማስወሰን ይሰበስባል ፡ ፲፩ የንብረት ባለቤት ለመሆን ፡ ውል ለመዋዋልና በስሙ ለመክሰስና ለመከሰስ ይችላል ፡ ፲፪• ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባሮችን ያከናውናል ። ፯ የኤጀንሲው አመራር ፩ ኤጀንሲው በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመንግሥት | - የሚሾም ዋና ሥራ አስኪያጅና አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ፡ ፡ ፪• ዋናው ሥራ አስኪያጅ የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከሚኒስትሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ | መሠረት የኤጀንሲውን ሥራዎች ይመራል ፡ ያስተዳ ድራል ፡ ፫ . የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከቱትን የኤጀን ሲውን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ ያውላል ፡ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ | ዓላማዎች ተከትሎ መንግሥት በሚያጸደቀው መመሪያ መሠረት የኤጀንሲውን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፡ ሐ ) የኤጀንሲውን የሥራ ፕሮግራምና በጀት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም ሥራ ላይ ያውላል ፡ መ ) ለኤጀንሲው በተፈቀደው በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፡ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ኤጀንሲውን ይወክላል ፡ ረ ) የኤጀንሲውን የሥራ አፈጻጸምና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ። ፩ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለአጀንሲው ሥራ ቅልጥፍና ባስፈለ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለኤጀ ንሲው ሠራተኛች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ሆኖም እርሱ በማይኖር ጊዜ ተክተእንዲሠራ የሚወከል ሰው ከ፴ቀናት ለሚበልጥ ጊዜየሚሠራነ ውክልናው አስቀድሞ በሚኒስትሩ መፈቀድ አለበት ። ፰ በጀት 6 የኤጀንሲው በጀት ከሚከተሉት የተውጣጣ ይሆናል ፤ ሀ ) በመንግሥት ከሚመደብለት የድጋፍ በጀት ፤ ለስ ከሚሰበሰበው የፈቃድ ክፍያ ፤ ሐ ) ኲማናቸውም ሌላ ምንጭ ። ጅ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ገንዘብ በኤጀንሲው ስም በሚከፈት የባንክ ሂሣብ ተቀማጭሆኖ | 2 ) The fund refered to in sub - Artice ( 1 ) of this Article የባለሥልጣኑን ሥራዎች ለማስፈፀም ወጪ ይሆናል ። ጅ ልልሂሣብ መዛግብት ፩ ኤጀንሲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት | ይይዛል ፣ ጅ የኤጀንሲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች / በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ክፍል ሦስት ስለፈቃድና የፈቃድ ሁኔታዎች ፫ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ፩ . ማንኛውም ሰው ከኤጀንሲው የተሰጠ ፈቃድ ሳይኖረው | 0 . የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለመስጠት አይችልም ። ጅ የቴሌኮሙኒኬሽን ሲስተም ወይም የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያዎችን ለፖሊስ ፡ ለጦር ኃይሎች ወይም ከሀገር | ደኅንነት ጋር በቀጥታ ለተያያዘ ሌላ አገልግሎት በመን | ግሥት እንዲውል ለማድረግ ፈቃድ አያስፈልግም ። ፩፩ የፈቃድ አይነቶች ፩ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለማካሄድየሚሰጥ ፈቃድ | 11 . Conditions of Licence ኤጀንሲው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ የተጠቀሰውን ዓላማ | ለማራመድ ያስፈልጋሉ ብሎ የወሰናቸውን ግዴታዎች ሊይዝ ይችላል ፡ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ የሚከተሉትን ግዴታዎች እንዲይዝ ሊደረግ ይችላል ፡ ሀ ) የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለገጠር ወይም ተለይተው ለሚወሰኑ አካባቢዎች እንዲደርስ ማድረግ ፤ ለ ) ከአገልግሎቱ ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን ፡ የውል ሁኔታዎችንና ግዴታዎችን በፈቃዱ ውስጥ በሚገ ለጸው መሠረትባለፈቃዱእንዲያሳትም የማስገደድ ፣ ሐ ) ለመንግሥትና ለተወሰኑ ተቋሞች የአገልግሎት ቅድሚያ መስጠት ፤ የአገልግሎቱን ታሪፍ ለመወሰን የሚያገለግሉ መመዘኛውን ፤ ሠ ) ለአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃዎችን ጨምሮ ባለፈቃዱ ሊከተላቸው የሚገቡ የቴክኒክ ደረጃዎ ችንና ተፈላጊ ሁኔታዎችን ። ፫ ኤጀንሲው ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከቴሌኮሙኒኬሽን ፈቃድ ጋር የተያያዙ ግዴታዎችን ሊያሻሽል ይችላል ። ገጽ ደጀሮቿ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፴፱ ዓ ም . Federal Negarit Gazeta No . 5 28 November 1996 – Page 278 ፲፪ የቴሌኮሙኒኬሽን ታሪፍ የመሠረታዊ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች ታሪፍ በኤጀ ንሲው ተጠንቶ ለመንግሥት እየቀረበ መጽደቅ አለበት ። - ፲፫ የቴክኒክ ደረጃዎች ፩ ኤጀንሲው የደንበኛ መገልገያ መሣሪያዎችን ጨምሮ ቴሌኮሙኒኬሽንን የሚመለከቱ የቴክኒክ ደረጃዎችን | ይወስናል ። ፪ ደረጃዎችን በሚመለከት የሚወጣው መመሪያ ኤጀንሲው በሚወስነው ሁኔታ ይታተማል ። ፲፩ መሣሪያዎችን ስለመፍቀድ ፩ ኤጀንሲው ከቴሌኮሙኒኬሽን ሲስተም ጋር ከመገጠ | 14 . Approval of Equipment ማቸው በፊት የኤጀንሲውን ፈቃድ የሚያስፈልጋቸውን የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያዎች ዝርዝር በመወሰን ለሕዝብ ያስታውቃል ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት መሣሪያዎች የኤጀንሲው ፈቃድ ያስፈልጋ ሀ ) የሬዲዮ ኮሙኒኬሽን መሣሪያዎች ፡ ለ ) ቲቪ : አርኦ ። ፫ ኤጀንሲው የመሣሪያዎችን ዓይነት ሲፈቅድ የሚከተ ሉትን መመዘኛዎች ማገናዘብ አለበት ፤ ሀ ) በሕይወትና በጤንነት ላይ አደጋ ያለማድረስ ሁኔታዎች ፣ ለ ) የመረጃ ጥበቃን ጨምሮ የቴሌኮሙኒኬሽን አውታር ጥገና ሁኔታ ፤ ሐ ) የኤሌክትሮማግኔቲክ መጣጣም ሁኔታ ፤ መ ) የኤሌክትሮማግኔቲክ ፍሪካንሲ ተገቢ አጠቃቀም ፣ ሠ ) በቴሌኮሙኒኬሽን አውታሩና በመሣሪያው መካከል የሚኖረው መጣጣም ፣ ረ ) ኤጀንሲው በመመሪያ የሚወስናቸው ሌሎች መመ ዘኛዎች ። ፬ የኤጀንሲው ፈቃድ የሚያስፈልጋቸውን የቴሌኮሙኒ ኬሽን መሣሪያዎች ኤጀንሲው በቅድሚያ ሳይፈቅድ ማምረት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ወይም ማከፋፈል የተከለከለ ነው ። ፲፭ ስለሬዲዮ መገናኛዎች ፩ ኤጀንሲው በዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት ለኢት | 15 . Radiocommunications ዮጵያ የተመደበውን የሬዲዮ ፍሪኳንሲ ለማስተዳደርና አጠቃቀሙን ለመፍቀድኃላፊ ይሆናል ። . ጀ ማንኛውም ሰው ከኤጀንሲው በተሰጠው ፈቃድ መሠረት ካልሆነ በስተቀር የሬዲዮ መገናኛ መሣሪያ ባለይዞታ ለመሆን ' ለመትከል ወይም ለማካሄድ አይችልም ። ፫ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ድንጋለፖሊስ ለጦር ኃይሎችና ለሌላ መንግሥታዊ አገልግሎት የሚውሉ የሬዲዮ መማሪያዎችን አይመለከትም ። ፲፮ ፍሪኳንሲ ስለመደልደል እ ኤጀንሲው ለቴሌኮሙኒኬሽን ለሬዲዮ መገናኛና | 16 . Assignment of Frequency ለሬዲዮና ቴሌቪዥን ሥርጭት አገልግሎት የሚውል ፍሪኳንሲ ይመድባል ፤ # ኤጀንሲው የፍሪኳንሲ አጠቃቀምን በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍደረጃ ያስተባብራል ፣ በትክክል ጥቅም ላይ መዋሉንም ይቀጣጠራል ፤ ገጽ 8ርህ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ኅዳር 10 ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም . Federal Negarit Gazeta - No . 5 28 November 1996 – Page 279 - ፫ . በፍሪኳንሲ ለመጠቀም በቀረበ ማመልከቻ ላይ ለመወሰን | 3 ) In deciding upon an application for assignment of የሀገሪቱ የወቅቱና የወደፊቱ ፍላጐት መገናዘብ ይኖርበታል ፡ # በተወሰነፍሪኳንሲየመጠቀም ፈቃድ በጊዜ ተወስኖ ለተለያዩ | ሰዎች ሊሰጥ ይችላል ። ፲፯ ቁጥጥር የማድረግ ሥልጣን ፩ ኤጀንሲው የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎችና በዚህ አዋጅ መሠረት የሰጣቸው ውሳኔዎች መከበራቸውን ለማረ ጋገጥ ኢንስፔክተሮችን ለመመደብ ይችላል ፡ ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የተመደበ ኢንስፔክተር የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሚያ ካሂድ ድርጅት ውስጥ ወይም ማንኛውም የሬዲዮ መገናኛ መሣሪያ ይኖራል ብሎ ለማመን በቂ ምክንያት _ _ bበሚኖረው ሥፍራ በሥራ ሰዓት ለመግባትና ቁጥጥር ለማደረግ ይችላል ፡ ፫ ኢንስፔክተሩ ማንኛውንም የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያ ለመመርመርና አግባብ ያላቸውን ሰነዶች ለማየትና ቅጂው እንዲሰጠው ለመጠየቅ ይችላል ፡ _ ፬• ኢንስፔክተሩ ቁጥጥር ወደሚያደርግበት ሥፍራ | ለመግባት የመታወቂያ ወረቀቱን ማሳየት አለበት ። ክፍል አራት ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመሬትና ሕንፃ ስለመጠቀም ፲፰ በመሬትና ሕንፃ ስለመጠቀም ፩ የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት ወደ ማንኛውም መሬት በመግባት የቴሌኮሙኒኬሽን መስመር ለመዘርጋት ፡ ለመጠገን ፡ ለማሻሻል ፡ ለመመርመርና ለመለወጥ ወይም መስመሩን ለማንሳት የሚያስፈልጉ ተግባሮችን ለማከናወን ይችላል ፡ ፪• የቴሌኮሙኒኬሽን መስመሩ የግድ በሕንፃዎች ላይ መዘር ጋትና ማለፍ ያለበት ሲሆን የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የሕንፃዎቹን ሁኔታ ሳያበላሽ መስመሩን ሊዘረጋ ይችላል ፡ • የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት በቴሌኮሙኒኬሽን መስመር ላይ ጉዳት ሊያደርስ ወይም እንቅፋት ሊፈጥር የሚችልን ማንኛውንም ዛፍ ወይም ቅርጫፍ መቁረጥ ይችላል ። ፩ . ማንኛውም የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) የተመለከቱትን ተግባሮች ለማከናወን ማንኛውም ስፍራ ከመግባቱ ከ7 ቀን በፊት ሊከናወኑ ስለታቀዱት ተግባሮች የሚገልጽ የጽሑፍ ማስታወቂያ ለመሬቱ ባለይዞታ ወይም ለሕንፃው ባለቤት መስጠት አለበት ። . ፭ የመሬቱ ባለይዞታ ወይም የሕንፃው ባለቤት ተቃውሞ ካለው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቅሬታውን ለኤጀንሲው ሊያቀርብ ይችላል ። ፮ ኤጀንሲው ለሁለቱም ወገኖች የመሰማት ዕድል - በመስጠት ተቃውሞን ከመረመረ በኋላ ተቃውሞን ጋለመቀበል ወይም የታቀደው ተግባር ያለአንዳች ገደብ ወይም ተገቢ መስሎ የታየውን ገደብ በማድረግ እንዲከ ናወን ሊፈቅድ ይችላል ። ገጽ Wጀት ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱የተ፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 5 28ጮ November 1996 – Page 280 ፲፬ . የቴሌኮሙኒኬሽን መስመርስለማስነሳት ወይም ስለማስለወጥ | 19 . Removal or Alteration of Telecommunication Line ፩ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፰ መሠረት የቴሌኮሙኒኬሽን መስመር የተዘረጋበት መሬት ባለይዞታ ወይም ሕንፃ ባለቤት በቂ ምክንያት ሲኖረው የቴሌኮሙኒኬሽን መስመሩ እንዲነሳ ወይም አዘረጋጉ እንዲለወጥ ለኤጀ ንሲው ሊያመለክት ይችላል ። ፪ : ኤጀንሲው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የቀረበለት ማመልከቻ በበቂ ምክንያት ላይ የተመሠረተ መሆኑንና የቴሌኮሙኒኬሽን መሥመሩን በሌላ አማራጭ ለመዘርጋት የሚቻል መሆኑን ሲያረጋግጥ መስመሩ እንዲነሳ ወይም አዘረጋጉ እንዲለወጥ ሊወስን ይችላል ። ፳ ስለ ካሣ ክፍያ ፩ የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት ለቴሌኮሙኒኬሽን መስመር በማንኛውም መሬት የመጠቀም ወይም መስመሩን በማ 1ይም መስመሩን በማ | 20 . Compensation . . . . . . : : . . . . . . . . ንኛውም ሕንፃ ላይ አሳልፎ የመዘርጋት ሥልጣኑን ሥራ ላይ ሲያውል ለሚያደርሰው ጉዳት ለመሬቱ ባለይዞታ ወይም ለሕንፃው ባለቤት ተገቢውን ካሣ የመክፈል ኃላፊነት አለበት ። ፪ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፱ መሠረት የቴሌኮሙኒኬሽን መስመር እንዲነሳ ወይም አዘረጋጉ እንዲለወጥ ያስደረገ ማንኛውም ሰው ለቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅቱ ተገቢውን ካሣ የመክፈል ኃላፊነት አለበት ። ፳፩ መሬትን ስለመውሰድ የተሌኮሙኒኬሽን ድርጅት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በግል የተያዘን መሬት በሕግ መሠረት ሊወስድ ይችላል ። ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፪ . ስለ ከተማ ፕላን 6 - የማንኛውም ከተማ ፕላን የቴሌኮሙኒኬሽን መስመ | 22 Town Plans ሮችን በግልጽ ለይቶ ማሳየት አለበት ። ፪ . ማንኛውም የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የቴሌኮሙኒ ኬሽን መስመር ሲዘረጋ የከተማውን ፕላን ተከትሎ የመዘርጋት ኃላፊነት አለበት ። ፳፫ ስለሌሎች ኮንስትራክሽኖች ፩ . ማንኛውም የኮንስትራክሽን ወይም የቁፋሮ ሥራ ወይም ቋሚነት ያለው ስትራክቸር ግንባታ በቴሌኮሙኒኬሽን መስመር አቅራቢያከመከናወኑ በፊት የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅቱን ስምምነትማግኘት ያስፈልጋል ። ፪ የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የስምምነት ጥያቄ ሲቀርብለት በ፴ ቀናት ውስጥ መልስ የመስጠት ግዴታ አለበት ። የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት በቀረበለት ጥያቄ ያላግባብ ሳይስማማ በመቅረቱ ለኤጀንሲው አቤቱታ ሲቀርብ ለትና ኤጀንሲውም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱት ሥራዎች በቴሌኮሙኒኬሽን መስመሩ ላይ ጉዳት የማያደርሱ ወይም የማያውኩ መሆናቸውን ሲያረ ጋግጥ ሥራዎቹ እንዲካሄዱ ሊፈቅድ ይችላል ። ፩ . ማንኛውምኮንስትራክሽን ወይምቋሚ የሆነ ስትራክቸር ግንባታ ከቴሌኮሙኒኬሽን መስመር ቢያንስ በሁለት ሜትር መራቅ አለበት ። ገጽ ፪፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፭ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 5 28 November 1996 – Page 281 ፭ አስቀድሞ የተዘረጋ የቴሌኮሙኒኬሽን መስመርን የሚያውክ ማንኛውም ግንባታ እንዲወገድ የቴሌኮሙኒ ኬሽን ድርጅቱ ቢያንስ የ፴ ቀናት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ባለቤቱን ወይም ባለይዞታውን ሊጠይቅ ይችላል ። ፮ የግንባታውባለቤት ወይም ባለይዞታ በተሰጠውየማስጠ ንቀቂያ ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ካላስወገደ የቴሌኮሙኒ ኬሽን ድርጅቱ ግንባታውን የማስወገድ መብት | 24 . Prohibitions ይኖረዋል ። ፳፬ ክልከላ ፩ በቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት ከተመደበ ሠራተኛ ወይም በኤጀንሲው ከተፈቀደለት ሰው በስተቀር ማንኛውም | ሰው የቴሌኮሙኒኬሽን መስመርን ማገናኘት ወይም ማለያየት የተከለከለ ነው ። ፪ በኮልባክ አገልግሎት መጠቀም የተከለከለ ነው ። ፳፭ ቅጣት ፩ : የዚህን አዋጅ አንቀጽ ፲፭ ( ፪ ) ወይም ፳፱ ( ፪ ) ድንጋጌ የተላለፈ ማንኛውም ሰው ከሁለት እስከ አምስት ዓመት | በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና እስከ ፲ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ፪ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ኤጀንሲውን ሳያስፈቅድ የሬዲዮ መገናኛ መሣሪ ያዎች ፡ የቲቪአርኦ መሣሪያዎች ወይም በኤጀንሲው መፈቀድ ያለባቸውን ሌሎች የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪ ያዎች ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው መሣሪያው በኤጀ ንሲው ይወረስበታል ። _ ፫• የዚህን አዋጅ ሌሎች ድንጋጌዎች የተላለፈ ማንኛውም ሰው በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት ይቀጣል ። ፳፮ የተሻሩ ሕጐች የሚከተሉት በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ፤ ፩ ቴሌፎን በእጅ መኖሩን ስለማስታወቅ የወጣው አዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፴፮ ፡ ፪ የቴሌፎን መገናኛ መስመር ጥበቃ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፬ / ፫• የቴሌኮሙኒኬሽን ቦርድማቋቋሚያ አዋጅቁጥር ፩፻፴፩ / ፳፮ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፷፱ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?