×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 18780

      Sorry, pritning is not allowed

በዚህ ጉዳይ ላሰበር ብየቅ
የሰበር መ / ቁ . 18780
ቀን ግንቦት 07/1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2 አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የኢት / ንግድ ባንክ
ተጠሪ፡ ከበቡሽ ጉልላት
ፍ ር ድ
የቀረበው ክርክር ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን /
ይወሰንልኝ / ን / የሚል ዳኝነት
የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / Cause of
action / አለው ? ወይስ የለውም ? ጉዳዩንስ ለመዳኘት የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ
ቦርድ ስልጣን አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን የህግ ነጥብ የሚመለከት ነው ፡፡
የም / ኦሮሚያ አሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ተጠሪ ላልተወሰነ ጊዜ
እንደተቀጠርኩ / ን / ይወሰንልኝ / ን / በማለት ያቀረቡትን ክስ በመቀበል አከራክሮ ውሣኔ
ሰጥቷል ፡፡ በውሣኔው ላይ
ይግባኝ የቀረበለት ይግባኝ
ሰሚው ፍ / ቤትም ከላይ
የተመለከተውን የህግ ነጥብ ሳይመረመር አልፎታል ፡፡
( ዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
መጠየቅ / ክስ » , , ,
አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር
ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተጠሪዎች ቀርበው የፀሐፊ መልስ
አቅርበዋል ፡፡
ችሎቱም ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን / ይወሰንልኝ / ን / የሚል ዳኝነት
በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / cause of action / አለው ? ወይስ የለውም ?
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን ስልጣን አለው ? ወይስ
የለውም ? የሚለውን የህግ ነጥብ መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ
መርምሯል ፡፡
ይህ ችሎት በመ.ቁ. 16273 ጥቅምት 22 ቀን 1998 በሰጠው ውሣኔ አግባብነት
ያላቸውን የህጉን ድንጋጌዎች በመተርጎም አንድ ሠራተኛ ከውሉና ከአሰሪና ሠራተኛ
ሕጉ አንፃር ሊያገኘው የሚገባና የቀረበት ጥቅም ካለ የቀረበት ጥቅም እንዲሰጠው
የሚችል ሲሆን ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ
በሚል ብቻ የሚቀርብን ክስ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድም ሆነ የሥራ ክርክር
ችሎት ተቀብለው ሊያዩ የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት የሕግ ትርጉም
ሰጥቷል ፡፡
በሌላም በኩል ቢሆን በመ / ቁ . 18180 አግባብነት ያላቸው የአሰሪና ሠራተኛ
አዋጅ ድንጋጌዎችን በመተርጎም የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የማየት ስልጣን
የተሰጠው የወል የሥራ ጉዳዮችን ነው ፡፡ አንድ የሥራ ክርክር የወል የሥራ ክርክር ነው
የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ
አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፡፡ በአንፃሩ አንድ የሥራ ክርክር
የወል ሳይሆን
የሥራ ክርክር ጉዳይ ነው የሚባለው የክርክሩ ውጤት
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
/ ግህና X
እ ' ' ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡ በተከራከረው ሠራተኛ ሠራተኞች / ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሲገኝ ነው በማለት የህግ ትርጉም ሰጥቷል ፡፡
በዚህ ጉዳይም የም / ኦሮሚያ አሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ተጠሪዎች ያቀረቡት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን / ይወስንልኝ / ን / በማለት ያቀረቡትን ክስ የክስ ምክንያት የሌለው ከመሆኑም በአሻገር የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል የሥራ ክርክር አይደለም ፡፡ በመሆኑም በሁለቱም ምክንያቶች የቀረበውን ክስ ውድቅ ማድረግ ሲገባው ጉዳዩን አከራክሮ በመወሰኑ መሠረታዊ የህግ ስህተት ፈጽሟል ፡፡
ው ሣ ኔ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመ / ቁ . 517/01/97 በታህሣስ 19 ቀን የሰጠው ውሣኔ እና ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ /
ቤት በመ / ቁ . 21525 በየካቲት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት
መዝገቡ ተዘግቷል ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?