×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 19552

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መ / ቁ . 19552
ቀን ሰኔ 19 ቀን 1998
ዳኞች፡- 1. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች፡- ሐረር ቢራ / ኤማ / ነፈጅ ቀርቧል ፡፡
መልስ ሰጭ፡- አቶ በለጠ ለይሶ አልቀረበም ፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር አንድ ሠራተኛ ከሥራ የተሰናበተው
በህገ ወጥ መንገድ መሆኑ
ወደ ሥራ እንዲመለስ በአዋጁ ቁ . 42/85
መሠረት ሲወሰን ከሥራ ከታገደበትና ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲመለስ
ውሣኔ እስከተሰጠበትና ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ ሊከፈለው
ይገባል ? ወይስ አይገባም ? የሚለውን ነጥብ የሚመለከት ነው ፡፡
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የሥር ፍ / ቤት መ /
ሰጭ ከሥራ የተሰናበተው በሕግ
ወጥ መንገድ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎ ወደ ሥራው እንዲመለስ የወሰነ ሲሆን
ውሣኔውን ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም አጽንቶታል ፡፡ አመልካች ይህን ውሣኔ በመቃወም
ለዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ
በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መ /
ሰጭ መልሱን አቅርቧል ፡፡
( ልል ጠቅላይ ፍርድ ሲቀ
ቅከል ልባጭ
ደመወዝ ስንሄ ስር
ችሎቱም አንድ ሠራተኛ ከሥራ የተሰናበተው በሕገ ወጥ መንገድ መሆኑ ተረጋግጦ ወደ ሥራ እንዲመለስ በአዋጅ ቁ . 42/85 መሠረት ሲወሰን ከሥራ ከታገደበትና ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲመለስ ውሣኔ እስከተሰጠበትና
ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ ሊከፈለው ይገባል ? ወይስ አይገባም ? የሚለውን ነጥብ መሠረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝቦ መርምሮታል ፡፡
ይህ ችሎት በመቁ . 17189 አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁ . 42 / 85 ን ድንጋጌዎች በመተርጎም ሕጉ ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል የሚፈቅድ አይደለም የሚል ውሣኔ ሰጥቷል ፡፡ በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ለመ / ሰጭ ውዝፍ
የተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ
ተገኝቷል ፡፡
ው ሣ ኔ
ይህ ችሎት መ / ሰጭ ውዝፍ ደመወዙ ሊከፈል አይገባም በማለት ወስኖ የሐረሪ
ብ / ክ / መ / የመ / ደ / ፍ / ቤት በመ.ቁ. 35/93 ጥቅምት 9 ቀን 1996 ዓ / ም የሰጠው
ውሣኔ እና የሐረሪ ብ / ክ / መ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ.ቁ. 97/96 ጥር 24 ቀን 1997
ዓ / ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽሏል ።
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
ተዘግቷል ፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
ዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ክል ግልባጭ

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?