×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 21133

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

$ 0 ጋራ ንብረት የሆነው ቤት ተይዟል ፡፡ ተጠሪም ዕዳው
የሰበር መ / ቁ 21133
ዳኞች ፦ 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ዓብዱልቃድር መሐመድ ጌታቸው ምህረቱ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ አመልካች ፦ የኢት / እህል ንግድ ድርጅት ተጠሪ፡ የአቶ ዋጋሪ ነቴ ባለቤትና ወራሾች
ፍ ር ድ ለሠበር አቤቱታ የቀረበበት ጉዳይ ባል ለገባው የግል ዕዳ ከባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት የሚስት ድርሻ ላይ ሊከፈል መቻል አለመቻሉን የሚመለከት ነው ፡፡
ሟች አቶ ዋጋሪ ዝነቲ በአመልካች ድርጅት ውስጥ በሚሠሩበት ጊዜ ባጎደሉት ገንዘብ ክስ ቀርቦባቸው ተፈርዶባቸዋል ። ይህን ፍርድ በማስፈፀም በተጀመረው የአፈፃፀም ክስ የሟችና የባለቤታቸው ( የተጠሪ ) ዕዳ ባለመሆኑ የጋራ ንብረታቸው የማይገባ መሆኑን ተከራክረዋል ፡፡
አፈፃፀሙን የያዘው የም / ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤትም እዳው በጋራ ኑሮ ወይም ለንግድ
ሥራ የዋለ ባለመሆኑ ከጋራ ንብረት ውስጥ የሚስትየው ድርሻ ላይ አፈፃፀሙ ሊቀጥል
አይገባም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል ። የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤትም የቀረበለትን የይግባኝ ቅሬታ
ሠርዞታል ፡፡
የሠበር አቤቱታውም የቀረበው በዚህ ትእዛዝ ላይ ነው ይህ ችሉትም የባል የግል ዕዳ
የባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት ከሚስትየው ድርሻ ላይ ሊከፈል ይገባል ወይስ አይገባም
የሚለውን ለመመርመር ተጠሪ እንዲቀርቡ ያደረገ ሲሆን ግራ ቀኙ የጽሑፍ ክርክር
አቅርበዋል ፡፡ ችሎቱም
አቤቱታ የቀረበበትን
ከተገቢው
ጋር አገናዝቦ
መርምሯል ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ቀን // - // - S
ንብረቶች በቶም ና
59 ( 2 ) ሥር ተቀምጧል ። በመሆኑም የአንደኛው ተጋቢ የግል ዕዳ ከፍ ሲል እንደተገለፀው የተጠሪ ባለቤት ባለእዳ የሆኑት በሥራ ላይ በነበሩበት ጊዜ ላጎደሉት ገንዘብ ነው የሥር ፍ / ቤቶችም በሟች ሚስት ድርሻ ላይ አፈፃፀሙ ሊቀጥል አይገባም ያሉት ዕዳው ለጋራ ጥቅም ወይም ለንግድ ሥራ አልዋለም በማለት ሲሆን ዋቢ ያደረጉትም የፍ / ሕ / ቁ 659 ( 2 ) ን ነው ። በመሆኑም የዚህን ድንጋጌ አጠቃላይ ይዘት ማየቱ ጠቃሚ ይሆናል ፡፡ የፍ / ሕ / ቁ 659 የማናገረው ስለ ባልና ሚስት ዕዳ ነው ። የድንጋጌው ንዑስ ቁጥር 1 ከባልና ከሚስቱ ከአንደኛው የሚጠየቅ ዕዳ ከግል ሃብቱ ላይ ወይም ከጋራ ንብረታቸው ሊጠየቅ እንደሚችል ያመለክታል ፡፡ በመሆኑም የባል ወይም የሚስት የግል ዕዳ ከባለዕዳው ተጋቢ የግል ሃብት ወይም ከጋራ ሃብታቸው ሊካፈል እንደሚችል ነገር ግን ከዚህ አልፎ ባለዕዳ ያልሆነውን ተጋቢ የግል ሃብት የማይመለከት መሆኑን እንረዳለን ፡፡ በሌላ በኩል ግን ዕዳው የባል ወይም የሚስት የግል ዕዳ ቢሆንም እንኳን ዕዳው የመጣው ለጋራ ጥቅም በሆነ ጊዜ በንዑስ ቁጥር 1 ሥር ከተመለከቱት
ባለዕዳው ባልሆነው ተጋቢ የግል ንብረት ላይም ሊከፈል የሚቻል መሆኑ በፍ / ሕ / ቁ
ለጋራ ጥቅም ወይም ለንግድ ሥራ አለመዋሉ ባለዕዳ ያልሆነውን ተጋቢ የግል ሃብት ከዕዳው
ነፃ ከሚያደርገው በቀር የተጋቢዎቹን የጋራ ንብረት ( ባለእዳ ያልሆነውን ተጋቢ ድርሻ
ጭምር ) በሚመለከት የሚያመጣው ለውጥ የለም ።
በተያዘው ጉዳይም የሟች ዕዳ ለጋራ ጥቅም የመጣ አይደለም የሚባል ቢሆን እንኳን
በፍ / ሕ / ቁ 659 ( 1 ) መሠረት ለዕዳው መክፈያ ከመዋል አያመልጥም ። በዚህም ምክንያት
የሥር ፍ / ቤቶች ለአፈፃፀም ከተያዘው የጋራ ንብረት ውስጥ የተጠሪዋ ድርሻ ለዕዳው
ሊከፈል አይገባም በማለት የሰጡት ትእዛዝ ስህተት ነው ፡፡
ው ሣ ኔ
1 / የምስ / ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 00881 በ 21 / 4 / 97 የሰጠው
ትእዛዝና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ 22645 በ 23 / 10 / 97 የሰጠው
ትእዛዝ ተሻሽሏል ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ቀን // - // - 3
2 / አፈፃፀሙ በተጠሪዋ ድርሻ ላይም ሊቀጥል ይገባል ።
3 / ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ፡ ።
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ይመለስ ።
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ቀን // - // -

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?