ተጠሪ በፌ / መ / ደረጃር !
የሰበር መ / ቁ 23868
ዳኞች፡ 1. አቶ ከማል በድሪ
ፍሥሐ ወርቅነህ ዓብዱልቃድር መሐመድ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካች ፦ ካይንድ ሐርትስ ሕፃናት መርጃ ልማት ድርጅት ነ / ፈጅ አለባቸው ፈጠነ ተጠሪ የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት አልቀረበም
ፍ ር ድ ይህ ጉዳይ ዕዳው እንደተከፈለ የሚቆጠርበትን የሕግ ግምት የሚመለከት ነው ።
ፍ / ቤት ባቀረበው ክስ አመልካች ከተጠሪ ተከራይቶ
ለተጠቀመበት ቤት ከነሐሴ 30 ቀን 1983 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 1987 ድረስ
ያለውን በወር ብር 604 ታስቦ 31,280 ብር ይከፈለን በማለት ጠይቀዋል ፡፡
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው ፍ / ቤትም አመልካች ክስ የቀረበበትን የኪራይ ገንዘብ
እንዲከፍል ወስኗል ፡፡ የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤትም የይግባኝ ቅሬታውን ባለመቀበል የሥር
ፍ / ቤትን ውሣኔ አጽንቷል ፡፡
የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን ይህ ችሎትም ከሁለት
ዓመት በላይ የሆነው የኪራይ ገንዘብ እንዲሠበሰብ ለመጠየቅ የሚችል መሆን አለመሆኑን
ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ሊቀርብ ይገባል በማለት የግራ ቀን የቃል ክርክር
አድምጧል ፡፡
ይህ ችሎትም መዝገቡን እንደመረመረው ተጠሪ ከ 30 / 12 / 83
ድረስ ያለው ኪራይ እንዲከፈል በመጀመሪያ ክስ ያቀረበው ነሐሴ 21 ቀን 1988 ነው ::
ይህ ክስ የቀረበበት ገንዘብም ከፊሉ ዕዳ መከፈል ከነበረበት ሁለት ዓመት በላይ እንደሆነው
መረዳት ችለናል ። ለጉዳዩ አግባብነት ያለው
የፍ / ሕ / ቁ 2024 ም በሁለት ዓመት
ያልተከፈለ ዕዳ እንደተከፈለ እንደሚቆጠር በዚህ ችሎት በመ / ቁ
ተሰጥቶታል ፡፡ በመሆኑም ተጠሪ የመጀመሪያ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ወደኋላ ያለውን
የሁለት ዓመት የኪራይ ገንዘብ ብቻ እንጂ እንዲከፈለው መጠየቅ የሚችለው ዕዳው
መጠየቅ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ያለፈውን ዕዳ ሊጠየቅ አይችልም ፡፡
ስለሆነም የሥር ፍ / ቤቶች በክስ የተጠየቀው የኪራይ ገንዘብ በሙሉ እንዲከፈል
መወሰኑ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል ፡፡
ው ሣ ኔ
1 / የፌ / መ / ጀ ፍ / ቤት በመ.ቁ 03965 በ 02 / 04 / 95 እና የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት
በመ / ቁ 16459 በ 04 / 07 / 98 የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሏል ፡፡
2 / አመልካች ከነሐሴ 21/86 እስከ ነሐሴ 21/88 ያለውን ኪራይ በወር ብር
604 ( ስድስት መቶ አራት )
ይክፈሉ ፡፡
3 / ወጪና ኪሣራ ግራ ቀ
ይቻቻሉ ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
You must login to view the entire document.