የመ / ቁ .17352
$ 19 ቁጥሮች 215 ፣ 320 / 2 / ፣ 207፣211 / 2 /
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ መቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ አመልካች፡- ዋዜማ የልብስና ሸራ መርቶች ኃ / የተ / የግ / ማህበር መልስ ሰጪ፡- የነገው ሰው ትምህርት አ / ማ
ለዳኝነት ስለሚከፈል
ከስነ ስርዓት ውጭ ስለሚቀርብ ክስ / ይግባኝ / የፍትሐብሔር ሥነሥርዓት
አመልካች ከስር ፍ / ቤት በመ / ሰጭ እንዲከፍለው የጠየቀው ወለድ በመ / ሰጭ
ሊከፈለው የሚገባ ቢሆንም አመልካች ክሱን ሲያቀርብ ለወለድ ጥያቄው የዳኝነት ክፍያ
ያልከፈለ በመሆኑ ወለድን በሚመለከት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመወሰኑና በዚህ አንፃር የቀረበውን መስቀለኛ ይግባኝ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ውድቅ ስላደረገው የቀረበ አቤቱታ
ው ሳ ኔ፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትና የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት በጉዳዩ የወለድ ክፍያን
በሚመለከት የሰጧቸው ውሳኔዎች ተሽረዋል ፡፡
1. አንድ ፍ / ቤት በሰጠው ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ የስነ ስርዓት ስህተት የፈጸመ እንደሆነ
ከተከራካሪ ወገኖች ጥያቄ ሲቀርብለት ወይም በራሱ አነሳሽነት ስህተቱን ማረም አለበት ፡፡
2 የስነ ስርዓት ስህተት ፈጽሞ እንደሆነ ጥያቄው ለፍ / ቤቱ ሳይቀርብ ይግባኝ ማቅረብ
አይቻልም ፡፡
. መዝገብ የቀረበለትን ጉዳይ መርምሮአል :: ለጉዳዩ መነሻ የሆነው
የሰበር መ / ቁ 17352
ሐምሌ 28 ቀን 1997 ዓ.ም ዳኞች መንበረፀሐይ ታደሰ
ፍሥሐ ወርቅነህ አብዱልቃድር መሐመድ ስንዱ ዓለሙ
መስፍን ዕቁበዮናስ አመልካች ዋዜማ የልብስና ሸራ ምርቶች ኃ / የተ / የግል ማኀበር መልስ ሰጪ የነገው ሰው ትምህርት አ / ማ
የሰበር ችሎት በዚህ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ /
ቤት የአሁኑ አመልካች እንዲከፈለው የጠየቀው ወለድ በስር ተከሣሽ ሊከፍል የሚገባው ቢሆንም ከሣሹ ክሱን ሲያቀርብ ከነሐሴ 16/91 ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ጥቅምት 27 ቀን 1994 ድረስ ያለውን ወለድ አስቦ ዳኝነት ስላልከፈለበት በዚህ ጊዜ ውስጥ የቀረበውን የወለድ ሂሣብ ፍ / ቤቱ አልተቀበለውም በማለት በመወሰኑ ነው :: ጉዳዩ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት መስቀለኛ ይግባኝ ቢያቀርብም ተቀባይነት ባለማግኘቱ ጉዳዩ ለሰበር ቀርቧል ፡፡
ጉዳዩ ለሰበር በመቅረቡ መልስ ሰጪ መልሱን ፣ አመልካች ደግሞ የመልስ መልሱን በጽሁፍ አቅርበዋል ፡፡ የአመልካች የሰበር ማመልከቻ በተከሣሽ እንዲከፈል የተጠየቀው ብር 562.966.74 ( አምስት መቶ ስልሣ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሣ ስድስት ከሰባ አራት ሣንቲም ) የወለድ ሂሣብ ዳኝነት አልተከፈለበትም ተብሎ መታለፉ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ያሳያል የሚል ሲሆን መልስ ሰጪ በበኩሉ በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለም የሚልበትን ምክንያት ዘርዝሮ አቅርቧል ፡፡ በዚህም መሠረት ለተጠየቀው ወለድ ዳኝነት ያልተከፈለበት መሆኑ ፣ በሌላው ጉዳይ የተከፈለ የዳኝነት ሂሣብ ለወለድ ጥያቄው ይያዝልኝ ማለት የማይቻል መሆኑ ፣ በሰበር በቀረበው ጥያቄ የመጨረሻ ውሣኔ የተሰጠው ጥቅምት 5 ቀን 97 ሲሆን በዚህም ላይ የቀረበ የሰበር አቤቱታ አለመኖሩ ፣ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበበት ጉዳይ በመስቀለኛ ይግባኝነት ቀርቦ ውድቅ የተደረገው በመሆኑ ተቀባይነት ሊኖረው እንደማይገባ በመግለጽ ተከራክሯል ፡፡ የመልስ መልስም ቀርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል ::
የሰበር ችሎት በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ አንድ ተሟጋች መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ሂሣብ ገቢ ሳያደርግ ክርክሩ እንደቀጠለ ፍ / ቤቱ የተገነዘበ እንደሆነ መፈፀም ያለበት ሕጋዊ ሥርዓት ምንድነው ? የሚለውን ጭብጥ የሚያስነሣ ሆኖ አግኝቶታል ::
የሕግ ትርጉም ወደሚያስፈልገው ዋናው ጉዳይ ከመሄዱ በፊት ፍርድ ቤቱ መልስ ሰጪ በመልሱ ላይ ያቀረባቸውን ነጥቦች ተመልክቷል ፡፡
መልስ ሰጪው ከስር ፍርድ ቤት የሂሣብ ይቀናነስልኝ ጥያቄ ስላልተነሣ ለሌላ ጉዳይ የተከፈለው ዳኝነት ለወለዱ ይጣጣልኝ የሚለው ጥያቄ በሰበር ሊታይ አይገባውም ብሏል :: ለፍርድ ቤት የሚከፈል ዳኝነት በአጠቃላይ ከሣሽ በሚጠይቀው ዳኝነት የሚታሰብ እንጂ ለእያንዳንዲ ርዕስ እየተለየ የሚጠየቅ ባለመሆኑ ክርክሩ የሚያስኬድ አይደለም :: ከዚህም በተጨማሪ ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ገቢ መሆን ያለበትን ሂሣብ የሚመለከት እንጂ በሁለቱ መካከል ያለውን ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከት ባለመሆኑ በአንዱ ወገን መነሣት አለመነሣቱ የሚያመጣው ለውጥ የለም ::
ከዚህ ሌላ በአመልካች የቀረበው የሰበር ማመልከቻ የመጨረሻ ውሣኔ ያልተሰጠበት መሆኑን በመጥቀስ ጥያቄው ውድቅ እንዲሆን ጠይቋል :: ሆኖም ለሰበር ችሎት የቀረበው ጥያቄ በመስቀለኛ ይግባኝ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ያጣ መሆኑን ከፍርድ ቤት ማኀደር ለመገንዘብ ችለናል :: ስለዚህ የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ አይደለም ሊባል አይችልም :: የአሁኑ መልስ ሰጪ ይግባኝ ጠይቄ በፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት ውሣኔ አግኝቻለሁ የሚለውም አሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበበትና ከክስ በፊት ያለውን የወለድ ሂሣብ የሚመለከት ሳይሆን ከውሣኔ በኋላ ያለውን ሂሣብ የሚመለከት መሆኑ “ ተገቢው ዳኝነት ተከፍሉበት ሣይጠየቅ ወይም ወደፊት ይከፈልበት ሳይባል ክስ ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ ዋናው ገንዘብ ተከፍሉ አለቀ ድረስ ወለድ ታስቦ ይከፈልበት በሚል መወሰኑ ትክክል ነው የምንለው አይደለም ከሚለው መልስ ሰጪው ራሱ በመልሱ ካካተተው የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት የውሣኔ ክፍል መገንዘብ ይቻላል ፡፡ ስለዚህ ሁለት የተለያዩ ጥያቄዎችንና ውሣኔዎችን በማምታታት ይኸው አሁን ለሰበር የቀረበው ጉዳይ የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ አይደለም በማለት የቀረበው አስተያየት ተቀባይነት ያለው አይደለም ::
ወደዋናው ጉዳይ ስንመለስ ይህ ችሎት የሕግ ትርጉም ያስፈልገዋል ብሎ የያዘው የሕግ ነጥብ የዳኝነት መክፈል የነበረበት ባለጉዳይ ሂሣቡን እንዳልከፈለ ፍ / ቤቱ ሲያረጋግጥ ሊሰጥ የሚገባው ውሣኔ ምንድነው ? የሚለው ነው አሁን በቀረበልን ጉዳይ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ / ቤት አመልካች የጠየቀው የወለድ ሂሣብ ለአመልካች መከፈል ያለበት ስለመሆኑ በፍርዱ ተቀብሎአል :: ፍርድ ቤቱ ከነሐሴ 16/91 እስከ ጥቅምት 27/1994
የሥነሥርዓት ሕግ 320
' ... ለማረም ግን ይግባኝ አንዱ ምናል + አ **
ድረስ ያለውን የወለድ ሂሣብ ብር 562,966.74 ውድቅ ያደረገው ከሣሹ ወለድ አስበው ዳኝነት አልከፈሉበትም በማለት ነው ::
ማንኛውም ለፍርድ ቤት ክስ የሚያቀርብ ሰው በሕጉ በተተመነው መሠረት የዳኝነት መክፈል እንዳለበት በሥነሥርዓት ሕጉ ቁጥር 215 ( 1 ) የተመለከተ ነው ፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ጉዳይ ሕጉ በሚያዘው መሠረት ከመቀጠሉ በፊት የሚመለከተው የፍርድ ቤቱ ክፍል ይህ አስተዳደራዊ የሆነ ተግባር መከናወኑን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል :: በሌላ በኩል በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት በሕጉ መሠረት የዳኝነት መክፈል የነበረበት ተከራካሪ ወገን ይህን ተግባር ሳይፈጽም ቢቀር ሕጉ ያስቀመጠው መፍትሄ ምንድነው ? የሚለውን ጥያቄ መመልከት አስፈላጊ ነው ::
የሥነ ሥርዓት ሕጉ በሙግት ሂደት የሚፈፀሙ ጉድለቶችን ለማረም የተለያዩ መፍትሄዎችን አስቀምጧል ፡፡ በዋናነትና በተለምዶ በብዛት ሥራ ላይ የሚውለው ጉዳዮችን ለይግባኝ ፍ /
ቤት እያቀረቡ ስህተቶች እንዲታረሙ መጠየቅ ነው :: ይህ የመፍትሄ አቅጣጫ አንድ በሙግት ሂደት የተፈፀመን ስህተት ስህተቱን ፈፀመ ለተባለው ፍርድ ቤት ሳይሆን በዕርከን የበላዩ ለሆነው ሌላ ፍርድ ቤት በማቅረብ የሚከናወን ሲሆን
በሙግት ሂደት የሚከሰቱ የመጨረሻው አማራጭ እንጂ ብቸኛው አማራጭ አለመሆኑ ከሕጉ አደረጃጀት ለመገንዘብ ይቻላል ፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ የሥነሥርዓት ሕግ ስህተቶችን ወደ ይግባኝ ፍርድ ቤት መውሰድ ብቻ ሳይሆን ጉዳዩን ስህተቱን ፈፀመ ለተባለው ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚቻልበትን ሥርዓት አስቀምጧል ፡፡ ከፍትሀብሄር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁ .320 ( 2 ) መገንዘብ እንደሚቻለው አንድ ፍርድ ቤት የገዛ ትዕዛዙን ለማሻሻል ፣ ለማረም ወይም እንደገና ለማጣራት በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ከሆነ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለው ይኸው ቅድመ ሁኔታ ከተሟላ ብቻ መሆኑ መረዳት ይቻላል ፡፡ አግባብነት ያለው የሕጉ ክፍል እንዲህ ይላል
በተሰጠው ፍርድ ወይም ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለማለት የሚቻል ቢሆንም እንኳ ፍርድ ወይም ትዕዛዝ የሰጠው ፍርድ ቤት በዚህ ህግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ፍርዱን ለማረም ለማሻሻል ወይም እንደገና ለማጣራት የሚችል ከሆነ
ይኸው ሥርዓት አስቀድሞ ሳይፈፀም ይግባኙን ማቅረብ አይፈቀድም :: ይህ ድንጋጌ አንድ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ወይም ፍርድ ራሱ መልሶ የሚያይበት ሥርዓት መኖሩንና ቀዳሚው የመፍትሄ አቅጣጫ ማንኛውንም ጉዳይ ወደ ይግባኝ ሰሚ ፍ /
ቤት መውሰድ ሳይሆን ጉዳዩን ለያዘው ፍርድ ቤት ለራሱ በማቅረብ
ተሠራ የተባለው ስህተት እንዲታረም መጠየቅ መሆኑ በግልጽ ያስቀምጣል :: ይህ አሠራር የይግባኝ ፍርድ ቤቶችን መጨናነቅ የሚቀንስ ከመሆኑ ባሻገር ተከራካሪ ወገኖች በአቅራቢያቸው ላለውና ጉዳዩን ለሚያውቀው ፍርድ ቤት ጥያቄአቸውን አቅርበው የተቀላጠፈ መፍትሄ የሚያኙበትን ሁነታ የሚያመቻች ፣ ጉዳዮች ባነሰ ጊዜና ወጪ እንዲስተናገዱ ዕድል የሚሰጥ አሠራር ነው ::
በሥነሥርዓት ሕጉ መሠረት ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍርድ ቤት በዚህ ሁኔታ መልሶ ቀድሞ ያያቸውን ጉዳዮች የሚያስተናግድባቸው በርካታ መንገዶች ቢኖሩም ( ለምሣሌ አንቀጽ 6፣74 ፣ 78፣358 አሁን ከቀረበልን ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነትና ተፈጻሚነት ያለው ግን የሥነሥርዓት ህጉ አንቀጽ 2 ዐ 7 ላይ የሠፈረው መሠረተ ሃሣብ ነው :: የዚሁ ሕግ ሙሉ ክፍል የሚከተለው ነው ::
በህግ ተለይቶ ካልተደነገገ ወይም ፍርድ ቤቱ በሌላ አኳኋን እንዲፈፀም ልዩ ትዕዛዝ ካልሰጠ በቀር በዚህ ሕግ የተመለከቱትን ውሣኔዎች ወይም በውሣኔዎቹ መሠረት የሚወጣውን ደንብ ባለመፈፀም ከሥነሥርዓት ውጭ የሆነ ክስ ሲቀርብ ወይም በክሱ ውስጥ ደንብ ውጭ የሆነ ተግባር ሲፈፀም ከተከራካሪዎቹ ወገኖች አንዱ ባመለከተ ጊዜ ወይም ፍርድ ቤቱ በራሱ ሥልጣን ይህ ከሥነሥርዓት ውጪ የቀረበው ክስ በከፊል ወይም በሙሉ እንዲሠረዝ ወይም ክሱ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በዚህም ምክንያት ስለሚደርሰው ኪሣራና ስለሌላውም ወጭ ተስማሚ መስሎ የታየውን ትዕዛዝ ይሠጣል ::
የዚሁ ሕግ የእንግሊዝኛ ቅጂ እንዲህ ይነበባል ፡፡
ከዚሁ የሥነ ሥርዓት ህግ መንደርደሪያ መርህ መረዳት እንደሚቻለው በማንኛውም ፍ / ቤት በሚካሄድ ክርክር ሥነሥርዓቱን ያልተከተለ ክስ የቀረበ እንደሆነ ወይም በክሱ ሂደት ሕጉ ያስቀመጣቸው የሥነሥርዓት ደንቦች በአግባቡ ያልተፈፀሙ እንደሆነ ፍርድ ቤት ሥርዓቱ ከሚያዘው ውጪ የተሠራውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሊሰርዝ
ይችላል ፡፡ ይህም የሚከናወነው በተከራካሪዎች አመልካችነት ብቻ ሳይሆን በፍርድ ቤቱ በራሱ አሳሽነትም ጭምር ነው :: በመሆኑም በዚህ መርህና ደንብ መሠረት በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች በሚያካሂዱት የዳኝነት ሥራ የሥነሥርዓቱን ደንብ ያልተከተለ ክንውን በራሳቸውም ሆነ በአስተዳደር ክፍሉ መፈፀሙን ሲያውቁ ወይም ሲደርሱበት ስህተቱን እንዲያርሙ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
በፍርድ ቤቶች አካባቢ የሚታየው የተለመደው አሠራር ዳኛ የሰጠውን ትዕዛዝ መቀየር አይችልም ፣ መቀየር የሚችለው የይግባኝ ፍርድ ቤት ብቻ ነው የሚል ቢሆንም ይህ በተለምዶ የዳበረው አሠራር የሥነሥርዓቱ ሕጉ ያሰፈረውን ከላይ የተጠቀሰውን መሠረታዊ መርህ የሚጻረር ነው :: ሥነ ሥርዓት ነክ የሆነን ጉዳይ የሚመለከት እስከሆነ ድረስ ባለጉዳዮች ወደይግባኝ ፍ / ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ስህተቱን ለፈፀመው ፍርድ ቤት ማመልከት ይፈቀድላቸዋል ፣ ዳኞችም እርግጥም ስህተት መሠራቱን ካመነበት ስህተቱን
ሥልጣንም አላቸው :: ( የሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁ .2 ዐ 9 )
ወደያዝነው
ጭብጥ ስንመለስ የከፍተኛ ፍ / ቤት ወለድን አስመልክቶ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ወለድ ሊከፈለው አይገባም በሚል ምክንያት ሳይሆን ለፍርድ ቤት ገቢ መሆን የነበረበትን የዳኝነት ሂሣብ አልከፈለም በማለት ነው :: የሥነሥርዓት ሕጉ ቁጥር 215 ( 1 ) እንደተደነገገው ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ ክሶች ሁሉ ዳኝነት ካልተከፈለባቸው በቀር ተቀባይነት አያገኙም :: ስለዚህ የዳኝነት ሂሣብ ለፍርድ ቤት ገቢ ማድረግ በክስ ሂደት መከናወን ያለበት ተግባር ነው :: የዳኝነት ክፍያ መጠናቀቅ ያለበት ክሱ ሲቀርብ እንደሆነ ከድንጋጌው ይዘት መገንዘብ ይቻላል ፡፡ በመሆኑም ይህን ሥራ እንዲያከናውኑ የተመደቡ የሚመለከታቸው የሚጠይቀውን ሥርዓት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል ፡፡ በሌላ በኩል መከናወን ያለበት ይህ ተግባር ሳይከናወን ቀርቶ ክሱ ለፍርድ ቤት ( ለዳኛን ቢቀርብ ክሱ ከሥነ ሥርዓት ወጪ የቀረበ ( procedurally irregular ) ይሆናል ፡፡ በፍትሐብሄር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 2 ዐ 7 እንደተደነገገው የሥነሥርዓት ሕጉን ወይም በሱ መሠረት የሚወጡ ደንቦችን በመጣስ የቀረበን ከሥነሥርዓት ወጪ የተፈፀመን ተግባር የማቃናት ሃላፊነት ለፍ / ቤቱ የተሰጠ በመሆኑ የሥነሥርዓት ግድፈት የተፈፀመ መሆኑ ሲታወቅ በዚህ መሠረት መከናወን ይኖርበታል ፡፡ በዚህ መሠረት ያልተከፈለ የዳኝነት ክፍያ ካለ የክሱን ሂደት አስመልክቶ የተፈፀመ የሥነ ሥርዓት ግድፈት መኖሩን ስለሚያመለክት ዳኞች በተጠቀሰው ሕግ መሠረት ግድፈቱን በማስተካከል ያልተከፈለ ሂሣብ ካለ ተሰልቶ እንዲከፈል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
ፍተኛ ፍ / ቤት የአሁኑ አመልካች ከ 16 / 12 / 91 እስከ ጥቅምት 27/1994 በያዝነውም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማድረግ የነበረበት ይህንን ነው :: አመልካች ወለድ እንዲከፈለው ጠይቋል :: ይኸው የአመልካች ጥያቄ በሕግ ተቀባይነት ያለው መሆኑንም ፍ /
ቤቱ ተቀብሎታል :: በመሆኑም ያልተከፈለ ሂሣብ ካለ በሥነሥርዓት ሕጉ ቁጥር 207 መሠረት ማስከፈል ሲገባው ይህን አልፎ የጠየቀውን ክስ በዚህ ምክንያት ውድቅ ማድረጉ ሕጉ ያስቀመጠውን የሙግት አመራር የተከተለ አይደለም ፡፡ በመሆኑም ይህ ፍርድ ቤት አልተቀበለውም :: የፍትሀብሄር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 211 ( 2 ) « ይግባኝ ሰሚ ፍ / ቤት ይግባኝ በተባለበት ጉዳይ ላይ የተፈፀመውን ማንኛውንም የሥነ ሥርዓት ጉድለት በራሱ አስተያየት ሊያርም በማለት ይደነግጋል ፡፡ በዚህም መሠረት የሰበር ችሎት የዳኝነትን አከፋፈል አስመልክቶ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈፀመውን የሥነ ሥርዓት ጉድለት ማቃናት እንዳለበት አምኖአል ::
1. የፌዴራል
ዓ.ም ያለውን የወለድ ክፍያ በሚመለከት በመዝገብ ቁ .11641 የሰጠውን ውሣኔ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት በመዝገብ ቁጥር 15574 የሰጠውን ውሣኔ ሽሯል :: 2. መልስ ሰጪ ከ 16 / 12 / 91 እስከ 27/2/94 ላለው ጊዜ በዋናው ገንዘብ ላይ 9 % ወለድ
ይከፈል ፡፡ 3. በዚሁ በተፈረደው የወለድ መጠን ያልተከፈለ የዳኝነት ገንዘብ አመልካቹ ለጠቅላይ
ፍ / ቤቱ ገቢ ያድርግ ፡፡ የውሣኔው ግልባጭ የሚሰጠው የዳኝነቱን ገንዘብ ገቢ
ማድረጉ ከተረጋገጠ በኋላ ነው ተብሏል ፡፡ 4. መልስ ሰጪ በዚህ ፍርድ ቤት ውሣኔ አመልካች ለዚህ ፍርድ ቤት ገቢ ያደረገውን
የዳኝነት ሂሣብ ይተካለት ፣ ሌላው በዚህ ፍርድ ቤት ያለውን ወጪና ኪሣራ ግራ
ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡ 5. ውሣኔያቸው ላይ ለውጥ መደረጉን እንዲያወቁት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትና
ለጠቅላይ ፍ / ቤት የዚህ ውሣኔ ግልባጭ ይላክ ፡፡
You must login to view the entire document.