$ አመልካች ላይ የመሰረተችውን ክስ ይመለከታል ፡፡
* መነሻ የሆነው
የሰበር መ / ቁ 21117
መጋቢት 13 ቀን 1998 ዓም ዳኛች ፦ መንበረፀሐይ ታደሰ
አብዱልቃድር መሐመድ ሓጎስ ወልዱ መስፍን እቁበዮናስ
ሒሩት መለሰ አመልካች ፦ ሙባረክ ሰማን ተጠሪ ፦ ሙንተሃ ዓብደላ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ ለአቤቱታው
ጉዳይ የተጀመረው በድሬዳዋ ናኢባ / የፌዴራል
መጀመሪያ ደረጃ ሸረዓ ፍ / ቤት ነው ፡፡ ክርክሩ ተጠሪ በሕገ ወጥ መንገድ ተይዞብብኛል
ያለችውን ቤት ይለቀቅላት ዘንድ
አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ካነሳቸው የመከራከሪያ ነጥባች አንዱ እና የመጀመሪያው
የናኢባ ፍ / ቤት ጉዳዩን ለመዳኘት የዳኝነት ስልጣን የለውም ። ክሱ መቅረብ ያለበት
ለመደበኛ ፍ / ቤት ነው ። የሚል ነበር ፡፡ ፍ / ቤቱ ግን የዳኝነት ስልጣን አለኝ በማለት ብይን
ከሰጠ በኋላ ፣ ወደክሱ ፍሬ ነገር ገብቶ በማከራከር ተከሣሽ ቤቱን ለከሣሽ ያስረክብ በማለት
ወስኖአል ፡፡ በዚህ ውሣኔ ላይ በየደረጃው ይግባኝ የቀረበላቸው የድሬዳዋ ፌዴራል ከፍተኛ
ሸሪዓ ፍ / ቤት እና የፌዴራል ጠ
ነይ ሸሪዓ ፍ / ቤትም
ውጭውን አጽንተዋል ፡፡ አቤቱታው
የቀረበው በዚህ ላይ ነው ::
ከመዝገቡ አጠቃላይ ይዘት እና ከግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር መገንዘብ እንደቻልነው
ተጠሪ አከራካሪው ቤት የአባቴ ነው :: አመልካች የያዘው በሕገወጥ መንገድ ነው ፡፡ በማለት
ስትከራከር አመልካች ደግሞ በዳኝነት ስልጣን ረገድ ካቀረበው መቃወሚያ በተጨማሪ ፣ ቤቱ
ፌዴራል በኛ ላይ ፥ ረድ .ት
ትክነፊ ግልባ
ቀን -- 1 1 / ፡
ወ / ሮ ሶፊያ ከተባለች ሰው የካቲት 6 ቀን 96 ዓ.ም በተደረገ የሽያጭ ውል ገዝቼ
የመንግሥት ግብር እየከፈልኩ የምኖርበት የራሴ ንብረት ነው ። በማለት የፍሬ ነገር ክርክር
አቅርቦአል ። አቤቱታው በሰበር ችሉት እንዲታይ የተደረገው የሸሪዓ ፍ / ቤቶች በጉዳዩ ላይ
ስላላቸው የዳኝነት ስልጣን በሚመለከት የቀረበውን አቤቱታ አግባብ ካለው ሕግ ጋር
አገናዝቦ ለመመርመር ነው ። በመሆኑም ወደጉዳዩ ፍሬ ነገር ዝርዝር ከመግባታችን በፊት
የሸሪዓ ፍ / ቤቶች ጉዳዩን ለመዳኘት ስልጣን አላቸው ወይ ? የሚውን ነጥብ መርምረናል ።
ፍርድ ቤቶች በሕግ የሚቋቋሙ እንደመሆናቸው የሚኖራቸው የዳኝነት ስልጣንም
የሚመነጨው ከሕግ ነው ፡፡ ማንኛውም ፍ / ቤት የቀረበላትን ጉዳይ ጉዳይ መስማትና
ሰምቶም ውሣኔ መስጠት የሚችለው በሕግ በግልጽ የተሰጠ የዳኝነት ስልጣን ሲኖረው ብቻ
ነው ። ስለዚህም ጉዳዩ ሲቀርብለት ከማንኛውም በፊት ሊያረጋግጠው የሚገባው በእርግጥም
በጉዳዩ ላይ የዳኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን ነው :: በተያዘው ጉዳይ ክሱ የቤት ይገባኛል
ጥያቄ የሚመለከት ከተከራከራዎቹ ወገኖች አንደኛው ማለትም ተከሣሹ በሸሪዓ ፍርድ
ቤቶች ለመዳኘት አልተስማማም ። ይልቁንም ግልጽ የሆነ መቃወሚያ አቅርቦአል ፡፡ በመሆኑም
ክሱን ያስተናገደው የኢባ / የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ሸሪዓት / ፍ / ቤት የዳኝነት ስልጣን
ነበረው ወይስ አልነበረውም ? ለሚለው ጥያቄ ከጉዳዩ ዓይነት እና ለጉዳዩ አግባብነት ካለው
ሕግ አንፃር አይቶ መልስ መስጠቱ ተገቢ ይሆናል ።
የሸሪዓ ፍ / ቤቶች በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕጉ እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች
ቁ 25 / 88
ከተመለከቱት
ፍርድ ቤቶች
የተደራጁ
እንደመሆናቸው የዳኝነት ስልጣናቸውም እንደዚሁ ራሱን በቻለ በተለየ ሕግ ነው ተመልክቶ
የሚገኘው ፡፡ በዚህ ረገድም የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶችና አቋም ለማጠናከር የወጣው
አዋጅ ቁ 188/92
ዋነኛው ተጠቃሽ ነው ፡፡
ረህ አዋጅ በክፍል ሁለት ስር የፍርድ
ቤቶች የወል የዳኝነት ስልጣን በዝርዝር ተቀምጦአል ፡፡ ለዳኝነት ስልጣኑ መሠረት ተደርገው
የተወሰዱት የጉዳዮች አይነት እና የተከራካሪዎቹ ወገኖች ስምምነት እንደሆኑም በሕጉ
ነተመልክቶአል ፡፡ እነዚህ በሸሪዓ ፍ / ቤቶች የዳኝነት ስልጣን ሥር እንዲሆኑ / እንዲታዩ /
በሕጉ የተመለከቱት ጉዳዮች እንደአግባብነቱ ሊስተናገዱ የሚችሉት ተከራካሪ ወገኖች
ፌደራል ቅላይ ፍርድ ቤት
ትነቴ ፅ ii3
የተመሠረተ በሕግ የሚታወቅ ግንኙነት የለም ፡፡ ለክርክሩ መነሻ የሆነው
በማድረግ በግዢ እንደሆነ በክርክሩ ላይ
ለመዳኘት እንዳልፈለገም ተረጋግጦኦል
በእስልምናው ሕግ ለመዳኘት ግልጽ በሆነ ሁኔታ ሲስማሙ / በፈቃዳቸው መርጠው የቀረቡ
ብቻ እንደሆነም
በአንቀጽ 4 / 2 /
ተደንግጎአል፡
በአንቀጽ 4 / 1 // ሀ /
የተመለከቱት ጉዳዮች በእስልምና ሃይማኖት ስርዓት የተፈጸመን ጋብቻ መሠረት ያደረጉ
የፍቺ ፣ የቀለብ አወሳሰን ፣ አካለመጠን ያልደረሱ ሕፃናት ሞግዚትነት የሚመለከቱ እና
በቤተሰብ ተዛምዶ ላይ የሚነሱ ሲሆኑ ፣ ጋብቻው በእስልምና ሃይማኖት ስርዓት የተፈጸመ
ባይሆንም ፣ ባለጉዳዮቹ ከእስልምና ሃይማኖት ስርዓት ለመዳኘት ፈቅደው ከሆነም ጉዳዩ
በሸሪዓ ፍ / ቤቶች ሊዳኝ ይችላል ፡፡ ሌሎቹ በአንቀጽ 4 / 1 / ለ / እና / ሐ / ሥር ያሉት
ስጦታ / ሂባ / ፣ የውርስ ወይም የኑዛዜ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ሲሆኑ ፣ በዚህ
ረገድም አውራሹ ወይም ስጦታ አድራጊው ወይም ተናዛዡ
ሙስሊም ሆኖ መገኘት
አስፈላጊ ነው ፡፡
ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ አመልካች እና ተጠሪ ሙስሊሞች ከመሆናቸው ወጪ
በመሃከላቸው
ጉዳይም የቤት ይለቀቅልኝ ክስ የሚመለከት ቢሆን ፣ አመልካች ቤቱን ሊይዝ የቻለው ውል
ተመልክቶአል ፡፡ አመልካች በእስልምና ሕግ
ከዚህ እንግዲህ መገንዘብ የሚቻለው በሕጉ
የተመለከቱት ለሸሪዓ ፍ / ቤቶች የዳኝነት ስልጣን መሠረት የሆኑት መስፈርቶች / የጉዳዩ
አይነት እና የባለጉዳዮቹ ፈቃደኝነት / አለመሟላታቸውን ነው ። የናኢባ / የፌዴራል
መጀመሪያ ደረጃ ሸረዓት /
ፍ / ቤት ጉዳዩን ለማየት የዳኝነት ስልጣን እንዳለው በመቁጠር
ክሱን የሰማው ይህን ግልጽ የሆነውን ሕግ እግምት ውስጥ ሳያስገባ በመቅረቱ እንደሆነም
መመልከት ይቻላል ፡፡ በመሆኑም አካሄዱ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ
አግኝተነዋል ፡፡
ው ሣ ኔ
1. በድሬዳዋ ናኢባ ፍ / ቤት በመ / ቁ 31/94 በ 5 / 11 / 96 ዓም ተሰጥቶ የድሬዳዋ
ፌዴራል ከፍተኛ ሸሪዓ ፍ / ቤት በ 20 / 8 / 97 ዓ.ም በሰጠው ውሣ እና የፌዴራል
ፌደራል ( 1 ላይ ናርድ ቤት
ተነ :: 3 ፡ 2 ፣ ጭ
ፊርማ // / 2 / 11
,, / 6 / ግ 8
ጠቅላይ ሸሪዓ ፍ / ቤት በመ / ቁ 9/97 በ 20 / 11 / 97 ዓም በሰጠው ትዕዛዝ ፀንቶ
የነበረው ውጭ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ 348 / 1 / መሠረት ሽረነዋል ።
2. ለአቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዳይ ላይ የሸሪዓ ፍ / ቤቶች የዳኝነት ስልጣን የላቸውም
ብለናል ፡፡
3. ወጪና ኪሣራን በተመለከተ
ግራ ቀኝ ወገኖች
የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡ መዝገቡ
ይመለስ ፡፡
ፌደራል ፡፡ 43 ኛ f ድ ቤት
ነል ግልባጭ
ፊርማ_ Ala
1 ) = { ጎ ፭
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
You must login to view the entire document.