የሰበር መ / ቁ . 22398
መጋቢት 20 ቀን 1998 ዓ.ም.
- የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡ ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
አብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ አሰግድ ጋሻው
መስፍን ዕቁበዮናስ አመልካች፡- አድነው አጵሎ ተጠሪዎች፡- 1. ሎላሳ ኢብሳ
2. ቴሬሳ ዱሬሳ
3. ጋዲሳ
መዝገቡን መርምረን
የሰበር አቤቱታው የቀረበው
የደቡብ ብ / ብ / ሕ / ክ / መ / ጠቅላይ ፍ / ቤት በመቁ .
10265 ጥቅምት 17 ቀን 98 ዓ.ም. በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ነው ፡፡ ጉዳዩ የተጀመረው
በክልሉ ቢማሻ ወረዳ ፍ / ቤት ነው ፡፡ ከሣሽ የነበረው የአሁኑ
አመልካች ሲሆን ፣
በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሠረተው ተከሣሾች በኔ ኃላፊነት ከመንግሥት መሥሪያ ቤት
በብድር የወሰዱትን ገንዘብ የከፈልኩ ስለሆነ ይህንኑ ይተኩልኝ በማለት ነው ፡፡ ክሱ
የቀረበለት የወረዳ ፍ / ቤት የሁለቱም ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ ፣ ከሣሽ በተከሣሾች ላይ
ክስ የመመስረት መብት የለውም
ምክንያት በመስጠት ክሱን ሰርዞአል ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትካከል ግልባጭ
► ጠላት ደግሞ ተጠሪዎች እሱ የከፈለላቸውን
በየደረጃው ይግባኝ እና አቤቱታ የቀረበላቸው የከፍተኛው እና የጠ / ፍ / ቤቱም የወረዳው
ፍ / ቤት የሰጠው ብይን ስህተት የለውም በማለት ሳይቀበሉት ቀርተዋል ፡፡
እኛም አመልካች ታህሣስ 20 ቀን 98 ዓ.ም. በፃፈው ማመልከቻ ያቀረበውን
አቤቱታ መሠረት በማድረግ ተጠሪዎቹን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል ፡፡ አቤቱታው
በሰበር ችሎት እንዲታይ የተደረገው አመልካች ክስ የመመስረት መብት የለውም
የሚለው የሥር ፍ / ቤቶች ብይን ከሕጉ ጋር ያለው አግባብነት ለመመርመር በመሆኑም
ይህንኑ ቀጥሎ ባለው ሁኔታ መርምረናል ፡፡
ከፍ ሲል እንዳመለከትነው አመልካች ክስ የመሰረተው ተጠሪዎች በሱ ኃላፊነት
ከመንግሥት መሥሪያ
ቤት በብድር የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱለት ነው ፡፡
በእርግጥም ገንዘቡ ከመንግሥት መሥሪያ ቤት በብድር የተወሰደ ስለሆነ ነው አመልካች
በስሙ ክስ ሊመስረትበት አይችልም የተባለው ፡፡ በበኩላችን እንዳየነው አመልካች ክስ
የመሰረተው የመሥሪያ ቤቱን ገንዘብ ለማስመለስ አይደለም ፡፡ የመስሪያ ቤቱ ገንዘብ ያዥ
በመሆኑ ምክንያት በሱ ኃላፊነት የተወሰደው ብድር ከራሱ ገንዘብ እንዲተካ መደረጉን
በመግለጽ ነው ክሱን ያቀረበው ፡፡ ይህ
ማለትም ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ነው የጠየቀው ማለት ነው ፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ
በዋነኛነት መታየት ያለበት ተጠሪዎች በአመልካች ኃላፊነት በብድር የወሰዱት ገንዘብ
ከመሠረቱ የአመልካቹ አልነበረም የሚለው ሳይሆን ፣ የክሱ ዓላማና በመጨረሻም
የቀረበው ጥያቄ ነው ፡፡ አመልካች የመስሪያ ቤቱን ገንዘብ አስመልሳለሁ በሚል
አልከሰሰም ፡፡ የአንድ ሰው የመክሰስ መብት የሚመነጨው ከሕግ ወይም ከውል ነው ፡፡
በተያዘው ጉዳይ አመልካች የከሰሰው ተገድጄ ከፈልኩ የሚለውን የራሱ ገንዘብ ዋናዎቹ
ባለዕዳዎች
የሚላቸው
ተጠሪዎች
እንዲተኩለት ነው ፡፡
በእርግጥም
አመልካች
የተጠሪዎችን ዕዳ ከፍሎ ከሆነ ይተኩለት ዘንድ በሕግ የተጠበቀ መብት አለው ፡፡ ይህም
ዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ልብ
ወረዳም
በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ / ቁ . 33 / 3 / እንደተመለተው አመልካች ከተጠሪዎች ላይ የሚጠይቀው ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑን ማረጋገጡን ነው በግልጽ የሚያሳየው ፡፡ የሥር ፍ / ቤቶች ብይን ክሱን ከዚህ አንፃር ያላየ በመሆኑ መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የሚታይበት ሆኖ አግኝተነዋል ፡፡ ስለዚህም መታረም አለበት ፡፡
ው ሣ ኔ 1. በወረዳው ፍ / ቤት በፍ / ክ / 124/96 በ25-4-97 ዓ.ም. ተሰጥቶ የከፍተኛው
ፍ / ቤት በፍ / ብ / ይ / መ / ቁ . 45/97 ሚያዝያ 19 97 ዓ.ም. እና የጠ / ፍ /
ቤቱም በይ / መ / ቁ . 10265 ጥቅምት 17 ቀን 98 ዓ.ም. በሰጡአቸው ትዕዛዞች ስህተት የለበትም የተባለው ብይን በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ / ቁ . 348 / 1 /
መሠረት ተሽሮአል ፡፡
ፍ / ቤት የአመልካችን ክስ በመቀበል ግራ ቀኝ ወገኖች በክሱ ፍሬ ነገር የሚያቀርቡት ክርክር በመስማት የመሰለውን ውሣኔ ይስጥ በማለት
በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ / ቁ .
መሠረት ጉዳዩ ይመለስለት ብለናል ፡፡
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትካከል ገልባጭ
You must login to view the entire document.