ኅ መጋ 3 የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
የሰበር መ.ቁ .22625
መጋቢት 14 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
አብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ተገኔ ጌታነህ
መስፍን ዕቁበዮናስ አመልካች፡- የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኤጀንሲ ተጠሪዎች፡- 1. በርሄ ታረቀኝ
2. ሠራዊት ታደሰ
መዝገቡን
ፍ ር ድ
የሰበር አቤቱታው አመልካች የፈረሰውን የስደተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት
ድርጅትን ወክለህ ክስ ልታቀርብ አትችልም ተብሎ በሥር ፍ / ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ
ላይ የቀረበ ነው ፡፡ ከመዝገቡ ማረጋገጥ እንደተቻለው አመልካች በፌዴራል መጀመሪያ
ደረጃ ፍ / ቤት ክስ የመሠረተው ከፈረሰው ድርጅት ጋር በተያያዙ ሁኔታዎች ለፍ / ቤት
ክስ አቅርቤ መከራከር እችል ዘንድ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ / ቤት የውክልና ሥልጣን
ተሰጥቶኛል በማለት ነው ፡፡ ክሱ የቀረበለት ፍ / ቤት የመክሰስ ችሎታ የለህም በማለት
የበየነው የውክልና ሥልጣን የለም በሚል ሳይሆን ፣ ከሣሽ በፈረሰው ድርጅት እግር
ተተክቶ የተጀመሩትን
ክርክሮች እንዲከታተልም ሆነ አዲስ
ክስ እንዲመሠረት
ውክልናው ሥልጣን አይሰጠውም የሚል ምክንያት በመስጠት ነው ፡፡ በዚህ ውሳኔ ላይ
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ርን_ MW
ቀን 1 2 “ ሪ
የቀረበው አቤቱታ በሰበር ችሎት ሊታይ እንደሚገባ ስለታመነበት ለችሎቱ ቀርቦ ግራ
ቀኝ ወገኖች ባሉበት ክርክሩ ተሰምቶአል ፡፡
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣኑ ያየው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ
ፍ / ቤት በሰጠው ብይን እንደተመለከተው የጠ / ሚ / ር ጽ / ቤት በቁ.መ. 470-1080 / 9
መጋቢት 24 ቀን 89 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ለአመልካች የውክልና ሥልጣን ሰጥቶአል ፡፡
ይህም አመልካች የፈረሰውን የስደተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትን የፍ / ቤት
ክርክሮች እንዲከታተል የሚያስችለው ነው ፡፡ አመልካች ይህን ውክልና በመያዝ ክስ
የመሠረተውም የመንግሥትን ጥቅም
አስጠብቀው
የስደተኞች
ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በፍትሐብሔር
በአንቀጽ
በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ከሚቋቋሙት ማህበሮች አንዱ ነው ፡፡ እነዚህን
ሲቋቋሙ ብቻ ሳይሆን ፣ ሲፈርሱም የፍትሐብሔር ድንጋጌዎቹ
መፅ ጋር
አግባብነት
በቁ .467 እንደተደነገገው
የፈረሰው
ንብረቶች
የመንግሥት ንብረት እንዲሆኑ የሚደረግበት ሁኔታም እንዳለ መገንዘብ ይቻላል ፡፡
በተያዘው ጉዳይ መንግሥት ከሣሽ ሆኖ የቀረበበት ምክንያትም ከዚህ ጋር በተያያዘ
ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል ፡፡ በእርግጥ የስደተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት
ድርጅት ንብረቶች ለመንግሥት ይሆናሉ ወይስ አይሆኑም ? የሚለው በጉዳዩ ፍሬ ነገር
ላይ ክርክር ከተደረገ በኋላ የሚወሰን ነው የሚሆነው ፡፡ በመሆኑም መንግሥት የውክልና
ሥልጣን በሰጠው አመልካች አማካኝነት ክሱን ያቀርብ ዘንድ መብት አለው ፡፡ ክስ
አታቀርብም ብሎ መከልከልም አግባብ አይደለም ፡፡ በዚህ ረገድ የፌዴራል መጀመሪያ
ደረጃ ፍ / ቤት የሰጠው ብይንም መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ፡፡
ዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ፊርማ \ AM
S -ሪ ና
ው ሳ ኔ
1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በመቁ .01079 በ18-12-96 የተሰጠው
ብይን እና ይህን ብይን በማፅናት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ.ቁ .37850
በ16-2-98 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ ተሽረዋል ፡፡
2. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት አመልካች ያቀረበውን ክስ መሠረት
በማድረግ የግራቀኝ ወገኖችን የፍሬ ነገር ክርክር እንዲሰማና በመጨረሻም
የመሰለውን ውሳኔ እንዲሰጥ ጉዳዩ ይመለስለት ብለናል ፡፡
መዝገቡ ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትክክል ግልባጭ
ሪ 2
ፊርማ_6
You must login to view the entire document.