የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አምስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፮ አዲስ አበባ - ታህሣሥ ፳ ቀን ፲፱፻፲፩ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፮ / ፲፱፻፶፩ ዓም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደግል ስለማዛወር የወጣ አዋጅ . ገጽ ፬፻፴፫ አዋጅ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፲፩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደግል ስለማዛወር የወጣ አዋጅ መንግሥት በኢኮኖሚው ዘርፍ ያለውን ሚናና ተሳትፎ በመለወጥና የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ድርሻ በማስፋፋት የአገሪቱን የኢኮኖሚ ልማት ማፋጠን አስፈላጊ በመሆኑ ፣ ይህንንም ለማድረግ በመካሄድ ላይ ያለውን የፕራይቬታይ | economic development of the Country , ዘሽን ፕሮግራም አፈጻጸም ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን | necessary to expedite the implementation of the ongoing ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የመንግሥት የልማት ድርጀቶችን ወደ ግል ስለማዘወር የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፮ ፲፱፻፲፩ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ ፕራይቬታይዜሽን ” ማለት የልማት ድርጅትን፡ የልማት ድርጅትን የተወሰነ ክፍል ወይምንብረት ወይም በንግድማኅበር ውስጥ በመንግሥት የተያዘን የአክሲዮን ድርሻ በሽያጭ ወደ ግል ማስተላለፍ ሲሆን ፤ ያንዱ ዋጋ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ • ፰ሺ፩ ገጽ ፬፻፴፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፮ታህሳስ ፳ ቀን ፲፱፻፵፩ ዓም : Federal Negarit Gazeta ሀ ) በግል ባለሀብቶች ተሳትፎ ለሚቋቋም የአክሲዮን ማኅበር የልማት ድርጅትን የመንግሥት መዋጮ ማድረግን እንዲሁም ለ ) የልማት ደርጅትን ማኔጅመንት ወደ ግል ማስተላ ይጨምራል ። ፪ “ የልማት ድርጅትን መሸጥ ወይም መዋጮ ማድረግ ” ማለት የልማት ድርጅትን የንግድ መደብርና ሀብት መሽጥ ወይም መዋጮ ማድረግ ነው ፤ ፫ . “ የልማት ድርጅት ” ማለት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፷፬ መሠረት የሚተ ዳደር የመንግሥት የልማት ድርጅት ወይም መንግሥት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ሲባል በመንግሥት የልማት ድርጅት የሰየመው ተቋም ነው ፣ ፬ . “ ኤጀንሲ ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፮ መሠረት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ፭ . “ ቦርድ ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳ ፩ ) የተመለ ከተው የኤጀንሲው ቦርድ ነው ፤ ፮ “ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ” ማለት የልማት ድርጅቶችን በአዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፳፬ መሠረት እንዲቆጣጠር በመንግሥት የተሰየመ አካል ነው ፤ ፯ « ባለአደራ ቦርድ » ማለት በአዋጅ ቁጥር ፲፯ / ፲፱፻፳፰ የተቋቋመው ወደግል ይዞታ የተዛወሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ነው ፤ ፰ « ባለሀብት » ፡ « የአገር ውስጥ ባለሀብት » እና « የውጭ ባለሀብት » ለሚሉት ቃላት በኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፳፰ የተሰጣቸው ትርጓሜ ይኖራቸዋል ፣ ሆኖም ፣ « የአገር ውስጥ ባለሀብት » መንግሥትና የመን ግሥት የልማት ድርጅቶችን አይጨምርም ። ፫ የፕራይቬታይዜሽን ዓላማዎች የአገሪቱ ፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፣ ፩ . መንግሥት ለሚያካሂዳቸው ገቢ ማስገኘት ፣ ፪ መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥያለውን ሚናና ተሳትፎ በመለወጥ ጥረቱን የመንግሥትን ትኩረት በሚጠይቁ ሥራዎች ላይ እንዲያውል ማስቻል ፣ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ እንዲስፋፋ በማገዝ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ልማት ማፋጠን ። አማት ሥራዎች የሚሆን ክፍል ሁለት ስለቅድመ ፕራይቬታይዜሽን ሥራዎች ወደግል ስለሚዛወሩ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል የሚዛወሩ የልማት ድርጅቶች ዝርዝር በተቆጣ ባለሥልጣን አቅራቢነት በመንግሥት ይወሰናል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት ወደ ግል እንዲዛወር ውሳኔ የተሰጠበት የልማት ድርጅት ማኔጅ መንት ከኤጀንሲው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ድርጅቱን ለፕራይቬታይዜሽን ለማዘጋጀት የሚያስ ፈልጉ እርምጃዎችን ሁሉ የመውሰድ ግዴታ አለበት ። ፭ የልማት ድርጅትን ወደ አክሲዮን ማኅበርነት ስለመለወለጥ ፩ ኤጀንሲው ለፕራይቬታይዜሽን ዝግጅት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው አንድን የልማት ድርጅት ወደ አክሲዮን ማኅበርነት እንዲለወጥ ሊያደርግ ይችላል ። ገጽ ፬፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ ታህሳስ ፳ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም . Federal Negarit Gazeta – በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት የሚቋቋመው አክሲዮን ማኅበር ካፒታል በአክሲዮኖች ተከፋፍሎ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት አክሲዮንነት ይያዛል ። ፫ . በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚቋቋም ወይም የልማት ድርጅትን የመንግሥት መዋጮ በማድረግ የሚቋቋም አክሲዮን ማኅበርን በሚመለከት የንግድ ሕጉ አንቀጽ ፫፻፲፪ / ፩ / ለ / እና ፫፻፲፭ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ አይሆኑም ። ፬ • ኤጀንሲው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት የተቋቋመ አክሲዮን ማኅበርን አክሲዮኖች ወደ ግል ማዛወር እስከሚጀምርበት ባለው የመሸጋገሪያ ጊዜ ሀ ) በንግድ ሕጉ ለባለአክሲዮኖች ጉባዔ የተሰጡ ሥልጣኖች ለተቆጣጣሪው ባለሥልጣን እንደ ተሰጡ ይቆጠራል ፣ ለ ) የአክሲዮን ማኅበሩ ዲሬክተሮች በሙሉ በተቆጣ ጣሪው ባለሥልጣን ይሾማሉ ፤ ሐ ) የንግድ ሕጉ አንቀጽ ፫፻፯ ፩ ፡ ፫፻፲፩፡ ፫፻፵፯ ፩ / እና ፫፻፵፱ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ አይሆኑም ; ሆኖም የንግድ ሕጉ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደአ ግባቡ ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ዋጋ ስለመተመን ፩ ኤጀንሲው የልማት ድርጅትን፡ የልማት ድርጅትን | 6 . የተወሰነ ክፍል ወይም ንብረት ወይም የመንግሥት አክሲዮንን ወደ ግል ለማዛወር በቅድሚያ ዋጋው እንዲ ተመን ያደርጋል ። ፪ • የዋጋ ትመና የሚከናወነው ቦርዱ ባወጣው የዋጋ ትመና መመሪያ መሠረት ይሆናል ። ፫ በዋጋ ትመናው መሠረት የሚወሰነው የመሸጫ መነሻ ወይም አመልካች ዋጋ በቦርዱ መጽደቅ አለበት ። ክፍል ሦስት ስለ ፕራይቬታይዜሽን ስልቶችና ከፕራይቬታይዜሽን ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ፯ . የፕራይቬታይዜሽን ስልቶች ፩ ኤጀንሲው አግባብነት ያላቸው የተለያዩ የፕራይቬታይ ዜሽን ስልቶችን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚቻልበትን ዝርዝር የአፈጸጸም ሁኔታ ያጠናል ። ፪ ለእያንዳንዱ የልማት ድርጅት የተመረጠው የፕራይቬታ ይዜሽን ስልት በቦርዱ መጽደቅ አለበት ። ፫ ለማንኛውም የፕራይቬታይዜሽን ስልት ተግባራዊ የሚደ ረገው የአፈጻጸም ሥርዓት በግልጽነት መርህ ላይ የተመ ሠረተ መሆን አለበት ። ፬ • በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭ / ፲፱፻፫፬ አንቀጽ ፴፱ / ፩ / -፭ / በተመለከቱት ምክንያቶች ሊፈርስ የሚችል የልማት ድርጅት በሌሎች የፕራይቬታ ይዜሽን ስልቶች ወደ ግል ሊተላለፍ ካልቻለ በአዋጁ አንቀጽ ፴፩ - ፭ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ሂሣቡ ተጣርቶ እንዲፈርስ ለማድረግ ለተቆጣጣሪው ባለሥልጣን የተሰጠው ሥልጣን በዚህ አዋጅ ለኤጄ ንሲው እንደተሰጠ ይቆጠራል ። የመክፈያ ገንዘብ ፩ : ኤጀንሲው የልማት ድርጅት ዋጋ በብር ወይም ተቀባ ይነት ባለው የውጭ አገር ገንዘብ እንዲከፈል ሊዋዋል ይችላል ። ገጽ ፬፻፴፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ ታህሳስ ፳ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም Federal Negarit Gazeta - No. 26 29 December , 1998- Page 936 የፍትሐብሔር ሕግ አንቀጽ ፩ሺ፪ፃ ድንጋጌ ቢኖርም የልማት ድርጅት ዋጋ መከፈል ያለበት በውሉ ላይ በተመለከተው ገንዘብ ነው ። ስለንብረት የእርጅና ቅናሽ ግብር የሚከፈልበትን ገቢ ለመወሰን ሲባል የሚታ ሰበው የንብረት የእርጅና ቅናሽ ስሌት የሚመሠረተው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ መሠረት በተሠራው የንብረቱ የዋጋ ተመን ላይ ይሆናል ፤ ሆኖም በጨረታ የተገኘው ዋጋ ዝቅ ያለ ከሆነ ስሌቱ የሚመሠረተው ገዥው በከፈለው ዋጋ ላይ ይሆናል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት የሚደረስ በትን የንብረቶች የዋጋ ዝርዝር ኤጀንሲው ለሚመለ ከተው የግብር ባለሥልጣን ያስተላልፋል ። ስለ ቴምብር ቀረጥ ወደ ገዥው የተላለፉና የንብረት ባለቤትነት ማስመዝ ገቢያ ሠነድን በሚመለከት የቴምብር ቀረጥ የሚከፈልባ ቸውን የንብረቶች ዋጋ ዝርዝር ኤጀንሲው ለሚመለ ከተው የታክስ ባለሥልጣን ያስተላልፋል ። በቴምብር ቀረጥ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲ / ፲፱፻፯ አንቀጽ ፭ / ፩ / የተደነገገው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ኤጀንሲው ያስተላለፈውን የንብረትዋጋዝርዝር በሚመ ለከት ተፈጻሚ አይሆንም ፲፩ የኢንቨስትመንት ሕጐች ተፈጻሚነት ነባር ድርጅትን ለማስፋፋትና ለማሻሻል ስለሚሰጡ ማበረታ ቻዎች እንዲሁም የውጭ ዜጐችና ባለሀብቶች በኢንቨስት መንት መስክ ስለሚሳተፉበት ሁኔታ ስለሚጠበቁላቸው መብቶች አግባብ ባላቸው የኢንቨስትመንት ሕጐች የተደነ ገጉት በፕራይቬታይዜሽን ለሚሳተፉ ባለሀብቶችም ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፲፪ • የሠራተኞችን የጡረታ ሽፋን ስለማስቀጠል ፩ . ማንኛውም የልማት ድርጅት ወደ ግል ከመዛወሩ በፊት የነበሩ የሠራተኞች የጡረታ ሽፋን ሳይቋረጥ ይቀጥላል ። የልማት ድርጅቱ አዲሱ ባለቤት ከሠራተኞች ጡረታ ጋር በተያያዘ አግባብ ባላቸው ሕጐች በአሠሪዎች ላይ የተጣሉ ግዴታዎችን ማክበር አለበት ። ፲፫ ስለ ልማት ድርጅቶች መብትና ግዴታ መተላለፍ ወደ ግል የተዛወረ የልማትድርጅትመብትና ግዴታዎች ወደ ገዢውይተላላፋሉ፡ ሆኖም እዳዎችን ለማስተላለፍ የአበዳሪዎችን ስምምነት ማግኘት ያስፈልጋል ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌ ቢኖርም ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሣቦች ወደ ገዢው እንደ ማይተ ላለፉ በሽያጭ ውሉ ውስጥ ስምምነት ከተደረገ ከዚሁ ጋር የተያያዙ መብትና ግዴታዎች ለባለ አደራ ቦርዱ ይተላለፋሉ ። ፲፬ • ስለ ድኅረ ፕራይቬታይዜሽን ክትትል ፩ በፕራይቬታይዜሽን የተሳተፈ ባለሀብት አሸናፊ እንዲሆን የተደረገው ያቀረበው የኢንቨስትመንት ፕላን ተቀባይነት በማግኘት ጭምር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፕላኑን በሽያጭ ውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ አለበት ። ፪ • ባለሀብቱ የኢንቨስትመንት ፕላኑን በሥራ ላይ ማዋሉን ለመከታተል የሚያስችሉ መረጃዎችን በየጊዜው ለኤጀ ንሲው የመስጠትና የኤጀንሲው ተወካዮችም በማንኛ ቸውም ጊዜ በድርጅቱ ውስጥ ተገኝተው ምርመራና ግምገማ እንዲያደርጉ የመፍቀድ ግዴታ አለበት ። ባለሀብቱ በዚህ አንቀጽ የተመለከቱትን ግዴታዎች ሳይወጣ ሲቀር የሚፈጸምበት ቅጣት በሽያጭ ውሉ በተወሰነው መሠረት ይሆናል ። ገጽ ፱፻፴፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፮ታኅሣሥ ፳ቀን ፲፱፻፵፩ ፲፭ ስለክርክር አወሳሰን ፩ . በኤጀንሲውና በፕራቬይታይዜሽን በተሳተፈ ባለሀብት መካከል የሚነሳ ክርክር በግልግል ዳኝነት እንዲታይ በውላቸው ውስጥ የተስማሙ ካልሆነ በስተቀር አግባብ ባለው የፌዴራል ፍርድ ቤት ይታያል ። ፪ • ተዋዋይ ወገኖች ክርክራቸው በግልግል ዳኝነት እንዲታይ የተስማሙ ከሆነ የግልግል ሥርዓቱ በውሉና አግባብ ባላቸው የፍትሐብሔር ሕግና የፍትሐብሔር ሥነ - ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ይመራል ። ክፍል አራት ስለ ፕራይቬይታዜሽን ኤጀንሲ እንደገና መቋቋም ፲፮ እንደገና መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁሟል ። ፪ : ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የኤጀንሲው ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈ ላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። የኤጀንሲው ዓላማ የፕራይቬታይዜሽኑ ፕሮግራም በዚህ አዋጅ መሠረት ቅልጥፍና ባለው ሁኔታ እንዲፈጸምማድረግ ይሆናል ። ሥልጣንና ተግባር ፩ በዚህ አዋጅ ሌሎች አንቀጾች የተደነገገው እንደተ ጠበቀ ሆኖ ፡ ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ -ሀ ) የፕራይቬታይዜሽኑፕሮግራም በዚህ አዋጅ ድንጋ ጌዎች መሠረት ያስፈጽማል ፤ ለ የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራሙ የሚመለከታቸው የልማት ድርጅቶች ወደ ግል የሚዛወሩበትን ቅደም ተከተል ይወስናል ፤ ሐ ) የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዛወር የሚያስ ፈልጉ ቅድመ ዝግጅቶች ሁሉ እንዲከናወኑ ያደርጋል ፤ መ ) በፕራይቬታይዜሽን የሚሳተፉ ባለሀብቶች የሚ ወዳደሩባቸውን መመዘኛዎች ይወስናል ፤ ሠ ) ፕራይቬታይዜሽኑን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ያዘጋጃል ፣ ረ ) በልማት ድርጅቶች ፕራይቬታይዜሽን ሊሳተፉ የሚችሉ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ሊበረታቱ የሚችሉባቸውን መንገዶች ይቀይሳል ፤ ሰ ) የፕራይቬታይዜሽኑ ፕሮግራምና አፈጻጸሙ በሕዝብ እንዲታወቅ ለማድረግ የሚያስፈልጉ እር ምጃዎችን ይወስዳል ፤ ሸ ) የድኅረፕራይቬታይዜሽን ክትትል በማድረግ በፕ ራይቬታይዜሽኑየተሳተፉ ባለሀብቶችየገቧቸውን ግዴታዎች ማክበራቸውን ያረጋግጣል ፣ ፕራይቬ ታይዜሽኑ ያስከተለውን አጠቃላይ ውጤትም ይገ መግማል ፣ ቀ ) የፕራይቬታይዜሽኑን ፕሮግራም ለማስፈጸም አግ ባብነት ከሚኖራቸው አከላት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመመሥረት የተቀናጀ እንዲኖር ያደርጋል ፣ በ ) የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ ውል ይዋዋላል ፤ በስሙ ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፤ ተ ) ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግ ባሮችን ያከናውናል ። ገጽ፱፻፴፰ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣቁጥርኝታኅሣሥ፳ቀን ፲፱፻፩ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta ፪ ) ኤጀንሲው የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራሙን አፈጻጸም ለማቀላጠፍአስፈላጊሆኖ ሲያገኘው አግባብነትያላቸው ተቋሞች የተወሰኑሥራዎችን በውክልናእንዲፈጸሙለት ሲያደርግ እንዲሁም ብቃት ካላቸው አማካሪዎች ጋር ተዋውሉማሠራት ይችላል ። ፳ የኤጀንሲው አቋም ኤጀንሲው ፤ የሥራ አመራር ቦርድ ፤ ፪ በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፳፩ ስለቦርድ አባላት ቦርዱ ሰብሳቢውን ጨምሮ በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። ቁጥራቸውም እንዳስፈላጊነቱ ይወሰናል ። ፳፪ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር በዚህ አዋጅ ሌሎች አንቀጾች የተደነገገው እንደተጠበቀ | 22. Powers and dties of the Board ሆኖ ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . የፕራይቬታይዜሽኑን ፕሮግራም አፈጻጸም በበላይነት ይመራል ፤ ይቆጣጠራል ፤ ፪ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ያወጣል ፤ ፫ • ከፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም አፈጸጸም ተያይዘው በሚነሱ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ እንደአግባቡ ውሳኔ ይሰጣል ወይም ከአስተያየቱ ጋር ለመንግሥት ያቀርባል ፤ ፩ . የፕራይቬታይዜሽኑ ሂደት ሥርዓትንና ሕጋዊነትን የተከተለ ፤ በአሠራር ግልጽነት መርህ ላይ የተመሠ ረተና የተቀላጠፈ መሆኑን ያረጋግጣል ፤ ፭ የኤጀንሲውን መዋቅርና የሥራ ፕሮግራም እንዲሁም ለመንግሥት የሚቀርበውን ዓመታዊ በጀትያጸድቃል ፤ ፮ • የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማ በመከተል የኤጀንሲው ሠራተኞች የሚተዳደሩበትን መመሪያ ያወጣል ፤ ለዋናው ሥራ አስኪያጅ ተጠሪ የሆኑትን የኤጀንሲውን ኃላፊዎች ቅጥርና ምደባ ያጸድቃል ፤ – ከፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራሙ አፈጻጸም ተያይዘው የሚቀርቡ አቤቱታዎችን መርምሮ አስተዳ ደራዊ ውሳኔ ይሰጣል ፤ ፰ የፕራይቬታይዜሽኑን ሂደት ለማፋጠን የሚረዱ አስፈላጊ እርምጃዎችን ሁሉ ይወስዳል ። የቦርዱ ስብሰባ ቦርዱ በወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ፤ ሆኖም አስፈላጊ | 23. Meetings of the Board ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢው ጥሪ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። ፪ ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በስብሰባ ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ቦርዱ ውሳኔ የሚያሳልፈው በድምጽ ብልጫ ይሆናል ፤ ሆኖም ድምፁ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ያለበት ወገን ሃሳብ የቦርድ ውሳኔ ሆኖ ያልፋል ። ፩ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ የራሱን የስብሰባሥነ ሥርዓትደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፳፬ የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ፩ ዋናው ሥራ አስኪያጅ የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኤጀንሲውን ሥራዎች ይመራል ፤ ያስተዳ ድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፤ ገጽ፱፻፴፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፮ታኅሠሥ፳ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም Federal Negarit Gazeta – ሀ ) በቦርዱ ስብሰባዎች በአባልነት ይሳተፋል ፣ ለ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ የተመለከቱትን የኤጀን ሲውን ሥልጣንና ተግባሮች ሥራ ላይ ያውላል ፤ ሐ ) ቦርዱ ።ደቀው መመሪያ መሠረት የኤጀንሲውን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ መ ) የኤጀንሲውን በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ ሠ ) ለኤጀንሲው በተፈቀደለት ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል ፤ ረ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ኤጀንሲውን ይወክላል ፤ ሰ የኤጀንሲውን የሥራ አፈጻጸምና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ። ፫ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለኤጀንሲው የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለኤጀ ንሲው ኃላፊዎችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተ ላልፍ ይችላል ፤ ሆኖም በማይኖርበት ጊዜ እርሱን ተክቶ የሚሠራው ኃላፊ ከ 30 ቀናት ለሚበልጥ ጊዜ የሚሠራ ከሆነ ውክልናው አስቀድሞ ለቦርዱ ቀርቦ መፈቀድ አለበት ። የኤጀንሲው በጀት በመንግሥት ይመደባል ። የሂሣብ መዛግብት ፩ ኤጀንሲው የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የኤጀንሲው የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይመው ኦዲተር ይመረመራሉ ። ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች የመተባበር ግዴታ ፩ . ማንኛውም የፌዴራል ወይም የክልል መንግሥት | 27. Duty to Cooperate መሥሪያ ቤት ወይም የመንግሥት ባለሥልጣን የፕራይቬ ታይዜሽን ፕሮግራሙን በማስፈጸምሂደትየሚጠየቀውን መረጃ ወይም ድጋፍ በመስጠት የመተባበር ግዴታ አለበት ። የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ለኤጀንሲው የሚተላለፉ መረጃዎ ችንና ለገዢዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች የሚቀርቡበት የጊዜ ገደብ ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ በተመለከተው መሠረት ይሆናል ። ፫ ከባለቤትነት መብት ፣ ከአገልግሎት ውሎችእናከፈቃድ ዝውውር ጋር በተያያዘ ገዥው ሊያሟላቸው የሚገቡ ፎርማሊቲዎች ባለመሟላታቸው የባከነ ጊዜ በሠን ጠረዡ ለተመለከተው የጊዜ ገደብ አይታሰብም ። ፳፰ ሕገወጥ ባለይዞታዎችን ስለማስለቀቅ ፩ ወደ ግል እንዲዛወሩ በተደረጉ የልማት ድርጅት ሕንፃዎች ወይም ቅጥር ግቢ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ በመኖር ርክክብ እንዳይፈጸም ያውካል የተባለ ሰውን ለማስለቀቅ የክስ አቤቱታ የቀረበለት ፍርድ ቤት የይዞ ታውን ሕጋዊነት የሚያመለክት መቃወሚያ ካልቀረ በለት በስተቀር በ፴ ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠትና ውሳኔውእንዲፈጸም ማድረግ አለበት ። ገጽ ፬፻፵ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ ታኅሣሥ፳ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓም Federal Negarit Gazeta – ፪ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ድንጋጌ ከአዋጅ ውጭ ስለተወሰዱ ንብረቶች በወጣው አዋጅ ቁጥር ፩፻፲ / ፲፱፻፷፯ መሠረት በኤጀንሲው ውሳኔ ለቀድሞ ባለቤቶቻቸው የሚመለሱ ንብረቶችንም በሚመ ለከት ተፈጻሚ ይሆናል ፤ ሆኖም የይዞታውን ሕጋዊነት የሚመለከት መቃወሚያ አይችልም ። ፳፱ የተሻሩና ተፈጻሚ የማይሆኑ ሕጐች ፩ የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፳፯፲፱፻፳፮ ( እንደተሻሻለ ) በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፪ : ይህን አዋጅየሚቃረን ማንኛውም ሕግ ፣ ደንብ ፣ መመሪያ ወይም የአሠራር ልምድ በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ፩ . የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ እና ፲፬ ድንጋጌዎች ከአዋጁ መውጣት በፊት ከኤጀንሲው ጋር ስምምነት የተደረገ ባቸው የሠራተኞች የጡረታ ሽፋን እና የኢንቨስት መንት ፕላን አፈጸጸም ክትትል በሚመለከትም ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፪ . የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፰ ፡ ፲ ፣ ፲፩ ፡ ፲፫ ፣ ፲፭ ፣ ፳፯ እና ፳፰ ድንጋጌዎች በአዋጅ ቁጥር ፳፯ / ፲፱፻፴፮ መሠረት ከተደረጉ ፕራይቬታይዜሽኖች ጋር ለተያያዙ ፍጻሜ ላላገኙ ጉዳዮችም ተፈጻሚ ይሆናሉ ። ፫ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌ ከዚህ አዋጅ መውጣት በፊት ከኤጀንሲው ጋር በሌላ አኳኋን ስምምነት የተደረገባ ቸውን ጉዳዮች የሚመለከቱ የውል ድንጋጌዎችን ተፈጸ ሚነት አያስቀርም ። ፴፩ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከታህሣሥ ፳ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ፣ ታህሣሥ ፳ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓም : ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ገጽ ፬፻፶፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፮ታኅሣሥ ፳ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta - No. 26 29 December , 1998Page 941 ሠንጠረዥ ከልማት ድርጅቶች ፕራይቬታይዜሽን ጋር በተያያዘ የሚሰጡ መረጃዎችና አገልግሎቶች የሚቀርቡበት የጊዜ ገደብ በተራ ቁ . የመረጃ አገልግሎት ዓይነት የጊዜ ገደብ [ የመሬት ይዞታን ማረጋገጥና የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ መስጠት የመሬት ሊዝ / ኪራይ ተመንን እና የሊዝ ውል ጸንቶ ሊቆይ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ የውሃ ክፍያ ተመኖች ማሳወቅ 15 ቀናት የተሽከርካሪ ባለቤትነት ማስተላለፊያ ሰነድ | 15 ቀናት የቤት ባለቤትነትና የመሬት ባለይዞታነት ማስተላለፊያ ሰነድ መስጠት የንግድ / የሥራ ፈቃድማዛወር መስጠት 15 ቀናት የቤት ኪራይ ፣ የመብራት ፣ የውሃ ወይም 15 ቀናት የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ውል ማዛወር የጉምሩክ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የገቡ ዕቃዎች የሚፈለግባቸውን የቀረጥ መጠን