×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 23173

      Sorry, pritning is not allowed

መዝገቡ ' ኣቅሪቦም s
የሰበር መ / ቁ 23173
ግንቦት 30 ቀን 1998 ዓም
ዳኞች ፥ መንበረፀሐይ ታደሰ
ሐጎስ ወልዱ
ተኔ ጌታነህ
መስፍን እቁበዮናስ
ሒሩት መለሰ
አመልካች አለቃ ደስታ ታፈረ
ተጠሪዎች ፦ 1. ወ / ሮ አብርሃት አርጋው
2. ካሉሱ ትኳበ
መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ በትግራይ ብ / ክ / መ / ጠ / ፍ / ቤት በመ / ቁ 02920/97
የሰበር አቤቱታው
በ 10 / 2 / 98 ዓ.ም ተሰጥቶ በክልሉ ጠ / ፍ / ቤት ሰበር ችሎት በመ / ቁ 11682 በ 4 / 3 / 98
ዓም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በተባለው ውሣኔ ላይ ነው ::
ከመዝገቡ እንዳየነው ጉዳዩ በንብረት / ሰብል / ላይ ደረሰ የተባለውን ጉዳት መነሻ
በማድረግ የተጠየቀ የካሣ ክፍያ የሚመለከት ነው ፡፡ ክርክሩ በተጀመረበት ወረዳ ፍ / ቤት
ከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሠረተው ሰብሌን በከብቶቻቸው
አስበልተው የብር 350 ኪሣራ ስላደረሱብኝ ይህን ገንዘብ ክርክሩ ካስከተለው ወጪ ጋር
ይክፈሉኝ በማ
ው ፡፡ የወረዳው ፍ / ቤት ጉዳዩ ቀደም ሲል በፍ / ቤት ክርክር ተደርጎበት
የመጨረሻ ውሣኔ አግኝቶአል ፡፡ የሚል ምክንያት በመስጠት ክሱን ውድቅ ሲያደርግ ፤ በዚህ
ላይ ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛ ፍ / ቤት ደግሞ የቀድሞው እና የአሁኑ ጉዳይ የተለያዩ
ናቸው ፡፡ በማለት ክስ የቀረበበት ገንዘብ ለከሳሽ እንዲከፈል ወስኖአል ፡፡ ከዚህ በኋላም ነው
ለአሁኑ አቤቱታ መነሻ የሆነው ውሣኔ በጠ / ፍ / ቤቱ የተሰጠው :: የጠ / ፍ / ቤቱም የወረዳው
ፌደራ፡ : 1 ** ይ ዓ t : [ .ት
የተሰጠውን ወደ ፍ / ቤት የሰጠውን ምክንያት በመስጠት / በመቀበል / በከፍተኛው ፍ / ቤት የተሰጠውን ውጫ ሽሮአል ።
አቤቱታው በዚህ ፌዴራል ጠ / ፍ / ቤት ሰበር ችሎት እንዲታይ የተወሰነው አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ቀደም ሲል የመጨረሻ ውጭ አግኝቶአል በሚል ተቀባይነት የማጣቱ አግባብነት ለመመርመር ነው ፡፡ በመሆኑም ይህን ነጥብ ከሥር ጀምሮ ከተደረገው የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እና ለጉዳዩ አወሳሰን አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝበን መርምረናል ፡፡
አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የመሠረተው በከብቶቻቸው ተበላብኝ ላለው ሰብል ካሣ እንዲከፈለው ነው ። የወረዳው ፍ / ቤት እና የጠ / ፍ / ቤቱ ጉዳዩ ቀደም ሲል የመጨረሻ ውሣኔ አግኝቶአል ለማለት የበቁት ከተሰወኑ ዓመታት በፊት በአመልካች እና በሁለተኛ ተጠሪ አባት መካከል ተደርጎ የነበረውን የንብረት / ተክል / ይገባኛል ክርክር እና በዚሁ ላይ
በአስረጂነት በመጥቀስ እንደሆነ ከውጫው ለመገንዘብ ችለናል ፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ቀድሞ ተደረገ የተባለው እና የአሁኑ ክርክር አንድ
ዓይነት ናቸው ወይ ? የሚለው እንደሆነ እናያለን ፡፡ ይህን ጥያቄ ለመመለስ ተገቢነት ያለው
ሕግ ደግሞ የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁጥር 5 ነው ::
አንድን ክስ ለሁለተኛ ጊዜ እንደቀረበ ተቆጥሮ ተቀባይነት ሊያጣ የሚችለው
በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ 5 / 1 / የተመለከቱት ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ ነው :: ይህም
ማለት በመጀመሪያ ደረጃ በሕግ ስልጣን የተሰጠው ፍ / ቤት ክርክሩን ተቀብሉ የመጨረሻ
የፍርድ ውሣኔ ከሰጠ በኋላ ሁለተኛው ክስ መቅረቡ መረጋገጥ አለበት ። በሁለተኛ ደረጃ
ደግሞ ቀድሞ በፍርድ የተወሰነው ክርክር ስረ ነገርና የተያዘው ጭብጥ በኋላ ከቀረበው
ክርክር ጋር አንድ ዓይነት ሊሆን ይገባል ። በሦስተኛ ደረጃ በሁለተኛው ክስ ተከራካሪ ሆነው
የቀረቡት ሰዎች ቀድሞ በተወሰነው ክስ ተከራካሪዎች የነበሩ ወይም ደግሞ ከነሱ መብት
ያገኙ ሶስተኛ ወገኖች መሆን አለባቸው ።
በተያዘው ጉዳይ እንደሚታየው ቀድሞ በተደረገው
ክርክር የተሰጠ የመጨረሻ
የፍርድ ውጭ እንዳለ እርግጥ ነው ። በዚህ በቀድሞው ክርክር የተያዘው ጭብጥና የክርክሩ
ፌያሪ ትኣያ ፍርድ ቤት
ስረ ነገር ግን በሁለተኛ ክርክር ስረ ነገርና ከተያዘው ጭብጥ ጋር አንድ ዓይነት አይደለም ።
የቀድሞው ክርክር ስረ ነገር የንብረት ይገባኛል ጥያቄን መሠረት ያደረገ ሲሆን ፣ በዚህ ረገድ
የተያዘው ጭብጥ ደግሞ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ንብረት / ተክል / የየትኛው ተከራካሪ ወገን
ነው ? የሚል ነው ። የሁለተኛው ክርክር ስረ ነገር ከውል ውጪ ስለሚደርስ ኃላፊነትን መነሻ
ያደረገ የካሣ ክፍያ ጥያቄ ነው ። በዚህ ረገድ መያዝ የሚገባው ጭብጥ / በከፍተኛው
ፍ / ቤት ውሣኔም እንደተመለከተው / ተጠሪዎች ከውል ውጪ ኃላፊነት በሚያስከትል ሁኔታ
በአመልካች ንብረተ / ሰብል / ላይ ጉዳይ አድርሰዋል ወይ ? ካሣስ የመከፈል ኃላፊነት
አለባቸው ወይ ? የሚል እንደሆነ መገንዘቡ አይከብድም ። በመጨረሻም በቀድሞው ክርክር
ተከራካሪ ወገኖች የነበሩት አመልካች እና የሁለተኛ ተጠሪ አባት ሲሆኑ ተጠሪዎችም አሁን
ከተያዘው ጉዳይ ጋር በተያያዘው ሁኔታ ከቀድሞ ተከራከሪ ወገሮች መብት ያገኙ ሶስተኛ
ወገኖቸ የሚባሉ አይደሉም ፡፡ በአጠቃላየ በቀድሞው ክርክር እና በሁለተኛው ክርክር
ምንም ዓይነት መመላለል ወይም ግንኙነት የለም :: በመሆኑም የጠ / ፍ / ቤት
የሰጠው ውሣ ሕጉን መሠረት ያደረገ ባለመሆኑ ውሳኔው መሠረታዊ የሕግ ስህተት
ያለበት ነው ለማለት ችለናል ፡፡
ው ሣ ኔ
1. በወረዳው ፍ / ቤት የተሰጠውን ውሣ በማጽናት በትግራይ ብ / ክ / መ / ጠ / ፍ / ቤት
በመ / ቁ 02920/97 በ10-2-98 ዓ.ም የሰጠው ውሣ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ
ቁ 348 / 1 / መሠረት ተሽሯል ፡፡
2. ተከራካ ወገኖች በዚህ ሰበርረ ክርክር ምክንያት ያወጡት ወጪም ሆነ የደረሰባቸው
ኪሣራ ይቻቻሉ ፡፡
3. ውሣኔው ለሥር ፍ / ቤቶች ይተላለፍ ፡፡ መዝገቡ ይመለስ ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
ፊርማ - 4 h

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?