ነጋሪት ጋዜጣ የጂኦሎጂ መረጃ መሰብሰብ ለሀገሪቱ የሶ እና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፪ አዲስ አበባ የካቲት ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፪ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፬ / ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ማቋቋሚያ አዋጅ - ገጽ ፩ሺ፪፻፵፪ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፬ / ፲፱፻፲፪ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ስለሀገሪቱ መልክዐ ምድርና ከመሬት በታች ስላለው ተፈጥሮ የሥነ ምድር መረጃዎችን መሰብሰብ ለኢንዱስትሪ ፡ ለኢነርጂና ለእርሻ መስፋፋት መሠረትና ወሳኝ በመሆኑ፡ የማዕድን ሀብትን መፈለግ ፡ መመርመር ዕድገት ጠቃሚ በመሆኑ ፡ ማናቸውንም የሀገሪቱን የሥነ ምድር መረጃዎች መሰብሰብ ፣ | mineral resources and collection of geological data is essen ማስቀመጥና በባለቤትነት መያዝ አስፈላጊ በመሆኑ ፣ ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ የኢት ዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይን ማቋቋም በማስፈለጉ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይን ማቋቋሚያ | Ethiopia , it is hereby proclaimed as follows : አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፬ / ፲፱፻፵፪ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ፩ “ ሥነምድር ” ማለት ምድርን ፣ ምድር የተገነባባቸውን ነገሮች ፡ በምድር ላይና በምድር ውስጥ የተከናወኑትን ወይም በመከናወን ላይ ያሉ ለውጦችንና ሌሎችን በመሬት ውስጥ የሚካሄዱ የተፈጥሮ ክስተቶችን የሚያጠና ሣይንስ ሆኖ በጂኦሎጂ ፡ በጂኦፊዚክስ ፣ በጂኦኬሚስትሪ : እንዲሁም በሌሎችም ዘዴዎች በመጠቀም ስለምድር የሚከናወኑ ጥናቶችን ይጨምራል፡ ያንዱ ዋጋ 2:30 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ . ፱ሺ፩ $ 6 ይ ( ከዚህ በኋላ “ ሰርቬይ ” | ገጽ ፩ሺ፪፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፪ የካቲት ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም. “ ምርመራ ” ማለት ማዕድናትን ለማግኘትና ልዩ ልዩ የሥነምድር መረጃዎችን ለመሰብሰብ በጂኦሎጂ ፣ በጂኦፊዚክስ፡ በጂኦኬሚስትሪ ፣ ወይም በሌሎችአመቺ የሥነምድር ሣይንስ ዘዴዎች በመጠቀም የሚካሄድ ሥራ ነው ። ፫ “ ስባት ” ማለት ክብደቱ ወይም ይዘቱ በታወቀና በተወሰነ የምድር አካል ውስጥ የሚገኝ የማዕድን መጠን ነው፡ ፬ . “ መረጃ ” ማለት ከጂኦሎጂካል ፡ ከሀይድሮጂኦሎጂካል፡ ከጂኦተርማል፡ ከጄኦፊዚካል ከጂኦኬሚካል ፣ ከቁፋሮና ከላቦራቶሪ ጥናት የተገኙማናቸውንም መረጃ ዎችን የሚያጠቃልል ሆኖ ሪፖርቶችን ፣ ካርታዎችን ፣ ፎቶግራፎችን : ፕላኖችን፡ ቻርቶችን ፡ ግራፎችን ፣ ሴክሽኖችን፡ ሎጐችን እንዲሁም የማዕድናት ፣ የድንጋ ዮችንና የሌሎች ናሙናዎችን ሁሉ ይጨምራል ፤ ፭ “ ማዕድን ” ማለት ማናቸውም ዋጋ ያለው የምድር ክፍል ሆኖ በምድር ላይ ወይም በምድር ውስጥ በተፈጥሮ ተከማችቶ የሚገኝ ነው፡ ፮ “ የማዕድን ሀብት ክምችት ” ማለት በአንድ በተወሰነ ሥፍራ በከርሰምድር ውስጥ በአካባቢው ከሚገኝ የማዕድን ስባትና መጠን በላይ በሆነ ሁኔታና ለምርት ብቁነት አለኝታ ያለው በተፈጥሮ ተሰብስቦ የሚገኝ የአንድ ማዕድን ወይም የስብስብ ማዕድናት ክምችት ፯ . “ ሚኒስትር ” እና “ ሚኒስቴር ” ማለት እንደቅደም ተከተ ላቸው የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትርና ሚኒስቴር ነው ፣ ፰ “ ሪሞት ሴንሲንግ ” ማለት ለምርመራ የሚውል በአውሮ | 3. Establishment ፕላንና በሰው ሰራሽ የመሬት ሳተላይት አማካይነት መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የጥናት ዘዴ ነው ። ፫ • መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል እየተባለ የሚጠራ ) ራሱን የቻለና የሕግ ሰውነት ያለው የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁሟል ። ፪ • ሰርቬዩ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የሰርቬዩ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላ | 5. Objective of the Survey ጊነቱ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ሊኖሩት ይችላል ። የሰርቬዩ ዓላማ የሰርቬዩ ዓላማ በሥነምድር ጥናት ዘዴዎች ስለምድርና በውስጧ ስለሚገኙ ማዕድናት ምርምር ማካሄድና ማናቸ ውንም የማዕድን ሀብት ክምችት መፈለግ ፡ መመርመር ፡ እንደአስፈላጊነቱም መገመትና ማዕድኑ የሚገኝበትን ድንበር ለይቶ ማመልከት ነው ። የሰርቬዩ ሥልጣንና ተግባር ሰርቬዩ የሚከተለው ሥልጣንና ተግባር ይኖረዋል ፤ ፩ . የጂኦሎጂ ካርታ ሥራ መሥራት ፣ ማዘጋጀትና ማተም ፣ ፪- የአየርና የመሬት ጂኦፊዚካልና የሪሞት ሴንሲንግ ጥናት ማካሄድ፡ ፫ • የማዕድን : የነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ ፣ የጂኦተ ርማል፡ የሀይድሮጂኦሎጂ እና የኢንጂነሪንግ ጂኦሎጂ መሠረታዊ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በየብስና በውሃ አካላት ላይ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የክምችቱን መጠን መገመትና ክምችቱ የሚገኝባ ቸውን ሥፍራዎች ድንበር ለይቶ ማመልከት፡ የሰርቬዩ ዋና ሥራ አስኪያዩ ገጽ ፩ሺ፪፻፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳ደ የካቲት ፳፰ ቀን ፲፱፻፪ ዓም • ፩ ዓላማውን ለማሳካት ባስፈለገ መጠን የእሳተ ገሞራ ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ፡ የመሬት መደርመስ ፣ የሚትዮ ራይት መውደቅና የመሳሰሉትን የተፈጥሮ ክስተቶችና ውጤቶችን የሚመለከት ጥናት ማካሄድ ፣ ውጤቱንም እንደሁኔታው ለሚያስፈልጋቸው ማሳወቅ ፣ ፭ በሰርቬዩ የአጭርና የረጅም ጊዜ የሰው ኃይል ፍላጐት መሠረት ሠራተኞችን ማሠልጠን ፣ ፮ የሥነምድር ሳይንስ ጥናትን በሚመለከት መረጃ መሰብሰብ ፣ በባለቤትነት መያዝ ፣ እንደአስፈላጊነቱ ዋጋ በማስከፈል ወይም ያለክፍያ ለተጠቃሚዎች ማቅረብ ፣ እንዲሁም መጽሔቶችን ማዘጋጀትና ማሠራጨት ፣ ፯ : ከሥራው ጋር አግባብ ያለውን መረጃ ሁሉ ከማንኛውም ምንጭ መጠየቅና ማግኘት፡ የሥነምድር ምርምርና ጥናትን በሚመለከት በማን ኛውም ስብሰባ ፡ ጉባዔና ሴሚናር ላይ መንግሥትን ወክሎ መሳተፍ ፡ ፬ ከመንግሥት በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት ለሚሰጠው አገልግሎት የአገልግሎት ዋጋ ማስከፈል ፣ ፲ የንብረት ባለቤት መሆን ፡ማስተላለፍ ፣ ውል መዋዋል ፣ በስሙ መክሰስና መከሰስ እና ዓላማውን ከግቡ ለማድረስ የሚያስፈልገውን ተመሳሳይ ተግባሮች ማከናወን ። ፯ . የሰርቬዩ ድርጅታዊ አቋም ሰርቬዩ ፣ ፩ አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፡ አንድ ዋና ጂኦሎጂስት፡ እና ፫ የሚያስፈልጉት ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ ስለዋናው ሥራ አስኪያጅ መሾም በሚኒስትሩ አቅራቢነት በመን ግሥት ይሾማል ። ፱ : ስለዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ዋናው ሥራ አስኪያጅ የሰርቬዩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ከሚኒስትሩ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የሰርቬዩ ሥራ በሚገባ ለመከናወኑ የበላይ ኃላፊ ይሆናል ። ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው ጠቅላላ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፤ ሀ ) በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት ሠራተ ኞችን ይቀጥራል ፡ ያስተዳድራል ፣ ያዛውራል ፣ ያሳድጋል ፣ ከሥራ ያሰናብታል ፤ ሆኖም የሰርቬዩ ሠራተኞች የደመወዝ ስኬልና የአበል መጠን መንግሥት በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚወሰን ይሆናል፡ ለ ) የሰርቬዩን የአጭር ፡ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ እያዘጋጀ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፤ ሐ ) የሰርቬዩን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፤ መ ) ለሰርቬዩ በተፈቀደው በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ) የሰርቬዩን የሥራ ክንውንና የሥራ እንቅስቃሴ የሚገልጽ ሪፖርት ለሚኒስትሩ ያቀርባል ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን ኣ ኣ ፈጸም አስፈላጊ ገጽ ፭ሺደኋ፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፱ የካቲት ፳፰ ቀን ፲፱ ዓም ረ ) የሰርቪዩን ዋና ጂኦሎጂስትና የመምሪያ ኃላፊዎችን በመምረጥ ለሚኒስትሩ አቅርቦ ያሾማል ፣ ሰ ) ሰርቪዩ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ሁሉ ሰርቬዩን ይወክላል ። ፫ ዋናው ሥራ አስኪያጅ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ የተመለከ ተውን የሰርቬዩን ሥልጣንናተግባርበሥራ ላይ ያውላል ። ፬ . ለሰርቬዩ የሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣ ተግባሩን ለዋናው ጂኦሎጂስትና ለሰርቬዩ ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። የዋናው ጂኦሎጂስት ሥልጣንና ተግባር ፩ . የሰርቬዩን የጂኦሳይንስ ጥናትና ተዛማጅ ሥራዎችን በበላይነት ይመራል ። ዋናው ሥራ አስኪያጅ በሌለበት ጊዜ እሱን ወክሎ ይሠራል ። የበጀት ምንጭ የሰርቬዩ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የሚገኝ ይሆናል ፤ ከመንግሥት የሚሰጥ ድጐማ ፣ ሰርቬዩ የሚያስከለው የአገልግሎት ዋጋና ሌሎች ክፍያዎች እና ከሌሎች ምንጮች የሚገኝ ገንዘብ ። የሂሣብ መዛግብት ስለመያዝ ፩ . ሰርቬዩ የተሟላና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብትና ሌሎች ገንዘብ ነክ ሰነዶችን ይይዛል፡ ፪ • የሰርቬዩ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሠነዶች ዋናው ወይም እሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። የተሻረ ሕግ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂ ጥናት ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር ፪፻፬ / ፲፱፻፸፭ በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሆኑትን ደንቦች ሊያወጣ ይችላል ። ፲፭ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፳፰ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ