የመ / ቁ . 14047
መልስ ሰጪዎች
© በአለ ይርጋ - የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ - የፌዴራ a m ቅላይ ፍርድ ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት ዳኞች : - አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ / ሮ ስንዱ አለሙ
ወ / ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች : - ዶ / ር ዳንኤል አለሙ
1. ወ / ሮ ሮማነወርቅ የማነብርሃን 2. ወ / ሮ በቀለች ወረደ ምስለአበባ ውቤ
የግዴታዎች መቅረት ገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቆጥሩ የህሊና ግምቶች
የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥሮች
አመልካች ታህሣሥ 1 ቀን 1981 ከመ / ሰጭዎች ጋር ባደረጉት የጥብቅና ውል መሠረት ለሰጡት የጥብቅና አገልግሎት የአገልግሎት ክፍያ ብር 46000 ( አርባ ስድስት ሺ ) እንዲከፈላቸው በ 1988 ያቀረቡትን ክስ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ክሱ ክፍያው መጠየቅ ከነበረበት ጊዜ ከሁለት ዓመት በኋላ የቀረበ በመሆኑ በፍ / ብ / ህ / ቁ 2024 ( ለ ) መሠረት እንደተከፈለ ይቆጠራል በሚል ውድቅ ስላደረገውና ውሳኔውን ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስላጸና የቀረበ አቤቱታ
ውሳኔ፡ - የስር ፍ / ቤቶች ውሳኔ ጸንቷል
1. በፍ / ብ / ሕ / ቁ 2024 በተደነገገው የሕግ ግምት ተጠቃሚ ያልሆነ ወገን ( ከሣሽ ክፍያው እንዳልተፈጸመ የማስረዳት ሸክም ያለበት ሲሆን ይኸን ሸክሙን መወጣት የሚችለው መሃላ በማውረድ ብቻ ነው ::
2. የሕሊና ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ደንብ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው ::
የሰበር ችሉት መዝ .14047 ሐምሌ 28 ቀን 1997 ዓ.ም
ዳኞች 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. » ፍሥሐ ወርቅነህ 3. » አብዱልቃድር መሐመድ 4. ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ 5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች መልስ ሰጭዎች
ዶ / ር ዳንኤል አለሙ ቀርበዋል 1 ኛ . ወ / ሮ ሮማነወርቅ የማነብርሃን 2 ኛ . ወ / ሮ በቀለች ወረደ 3 ኛ . ወ / ሮ ምስለአበባ ውቤ
በክርክሩ አልቀረቡም
መዝገቡ ተመርምሮ
ውሣኔ ተሰጥቷል ፡፡
አመልካች የሰበር አቤቱታውን ያቀረቡት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በሰጠውና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ባፀናው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ነው ::
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ጉዳዩን አይቶ ውሣኔ የሰጠው አመልካች መልስ ሰጭዎች በፍርድ ቤት ያላቸውን የተለያዩ ጉዳዮች በተለያዩ መዝገቦች እነሱን ወክዬ እንድከራከር ወክለውኛል ፤ የጥብቅና ውሉም ታህሣሥ 1 ቀን 1981 ተፈርሟል ፤ በውሉም መሠረት ለፈፀምኩት የጥብቅና አገልግሎት በአጠቃላይ ብር 46 , ዐዐዐ ( አርባ
ስድስት ሺህ ) ይከፈለኝ በማለት ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው :: መልስ ሰጭዎች በሰጡት መልስ ውሉ የተፈፀመው በ 1981 ሲሆን ክሱ ግን የቀረበው በ 1988 ነው ፤ ይሄም የተጠቀሰውን ክፍያ ሳንጠየቅ ሁለት ዓመት ያለፈ በመሆኑ በፍ / ብ / ህ / ቁ .2024 ( ለ ) መሠረት ክፍያው እንደተፈፀመ ይቆጠራል በማለት የተከራከሩ ሲሆን ሌሎች ክርክሮችንም አንስተዋል :: ፍርድ ቤቱም መልስ ሰጭዎች ክፍያውን በጽሁፍ አላመኑም ፤ ክሱ ከሁለት አመት ገደቡ በኋላ በመቅረቡ በፍ / ብ / ህ / ቁ .2024 ( ለ ) መሠረት የህሊና ግምት እንዳይወሰድ እንዲሰጡ አልጠየቁም ፤ በመሆኑም
► 1. መታየት ያለበት በፍ / ብ / ህ / ቁ .2 ዐ 24 ( ለ ) መሠረት ክፍያው መፈፀሙን የህሊና ግምት ወስዷል በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎታል ፡፡ ይህንኑ ውሣኔ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትም በይግባኝ ተመልክቶ አጽንቶታል ::
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በተጠቀሰው ውሣኔ ላይ ሲሆን ይዘቱም ሲጠቃለል አመልካች የጥብቅና አገልግሎት የሰጠሁት በተለያዩ መዝገቦች ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ ጥያቄውም እንደየችሎቱ የክርክር ሂደት ጉዳዮቹ ተጠቃልለው ውሣኔ ሲያገኙ መቅረብ የሚገባው በመሆኑ ጥያቄው በዚሁ መሠረት ቀርቧል ፤ መልስ ሰጭዎች የጥብቅና ውሉን መፈፀሙን አልካዱም ፧ የፍ / ብ / ህ / ቁ .2 ዐ 24 ሊፈርስ የሚችል የህሊና ግምትን የያዘ ነው :: በመሆኑም በፍ / ብ / ሕ / ቁ .2025 እና ተከታታዮቹ የህሊና ግምቱ እንዳይወሰድ ( ለማፍረስ ) ያቀረብኩትን ክርክር ፍ /
ቤቱ ሊመለከትልኝ ይገባ ነበር ፤ ስለሆነም የስር ፍ / ቤት ውሣኔ መሠረታዊ የህግ ስህተት ስለፈፀመበት እንዲሻር የሚል ነው ::
መልስ ስጭዎች ቀርበው መልስ እንዲሰጡ የጋዜጣ ጥሪ ተደርጎ ባለመቅረባቸው ፍርድ ቤቱ በአመልካች በኩል የቀረበው ማመልከቻ ብቻ መሠረት በማድረግ ውሣኔ ሰጥቷል ፡፡ በቀረበው
በፍ.ብ.ሕ.ቁ .2 ዐ 24 የሰፈረውን የሕሊና ግምት አመልካች በመሠረተው ክስ ላይ ተፈጻሚ ያደረጉት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም ? የሚል ነው ፡፡ አመልካች በመጀመሪያው ፍርድ ቤት በ 1981 ዓ.ም ከመልስ ሰጪዎች ጋር በመሰረትነው የጥብቅና ውል መሻነት ላበረከትኩት አገልግሉት ብር 46 , ዐዐዐ ( አርባ ስድስት ሺህ ) ይከፈለኝ የሚል ነው ፡፡ ከክሱ ይዘት ለመመልከት እንደሚቻለው አመልካች ከመልስ ሰጪዎች የሚፈልጉት ክፍያ የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ ነው :: አመልካች ክስ ያቀረቡት መልስ ሰጪዎች ከውሉ የሚመነጨውን የክፍያ ግዴታቸውን አልተወጡም በሚል ነው :: የጥብቅና አበል መከፈል አለመከፈሉ አከራካሪ በሆነ ጊዜ የማስረዳት ሸክሙ የማን ነው ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ የማይቀር ነው :: የፍትሀብሄር ሕግ ቁጥር 2 ዐ 24 ( ለ ) ከሁለት ዓመት በላይ የሆነውን የጥብቅና ክፍያ በሚመለከት የሕሊና ግምት በማስቀመጥ የውል የመክፈል ግዴታ ያለበት ወገን እንደከፈለ ይቆጠራል በማለት የህግ ግምት ተጠቃሚ ያደርገዋል ፡፡ በሌላ በኩልም በሕጉ 2026 ( 1 ይህን የህሊና ግምት ማፍረስ እንደማይቻልና ለጥብቅና አገልግሎት ክፍያ አልተከፈለኝም የሚል ወገን ብቸኛ ግምቱን የማፍረሻ አማራጭ መሃላ እንዲወርድለት መጠየቅ ብቻ መሆኑን ያስቀምጣል ::
የህሊናውን በ
በዚህ መሠረት መከፈል ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ወይም ክፍያውን ያልጠየቀ ተዋዋይ በውሉ መሠረት የሚገባውን ክፍያ እንዳገኘ የመገመት ብቻ ሳይሆን ክፍያው እንዳልተከፈለው የሚያስረዳበት የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓትም ሌላ ፍሬ ነገርን ለማስረዳት ከሚከተለው ሥርዓት የተለየ ይሆናል :: በመደበኛ የሙግት ሂደት የማስረዳት ሸክም ያለው ወገን እንዲያስረዳ የሚጠበቅበትን ፍሬነገር ለማስረዳት ብዙም የሕግ ገደብ የለበትም :: ፍሬ ነገሩን ያስረዳልኛል የሚለውን ማንኛውንም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ ይችላል :: የጽሁፍ የሰው ወይም የአካባቢ ማስረጃ በማቅረብ የማስረዳት ሸክሙን ሊወጣ ይችላል :: በፍትሀብሄር ሕጉ 2024 የሚሸፈን ፍሬ ጉዳይ ባጋጠመ ጊዜ ግን የማስረዳት ሸክሙ ከአንድ ወገን ( ከተከሣሽ ወደሌላው ( ወደከሣሽ ከመዘዋወሩ በተጨማሪ የማስረዳት ሸክሙን መወጣት የሚቻልበት የማስረጃ ዓይነትም ውሱን ነው :: በ 2026 መሠረት የማስረዳት ሸክም የተሸጋገረበት ከሣሽ ይህን የማስረዳት ሸክሙን መወጣት የሚችለው መሃላ በማውረድ ብቻ ነው :: ሌላ የትኛውም ዓይነት ማስረጃ ቢሆን
ሊያፈርሰው አይችልም ::
በዚህ ህግ የሰፈረው የህሊና ግምት ከይርጋ ሕግ ጋር የሚያያዝ አይደለም ፡፡ በ 2 ዐ 24 የሠፈረው የሕሊና ግምት የማስረዳት ሸክም ከተከሣሽ ወደከሣሽ ያዞራል ፣ የማስረዳት ሸክም የዞረበት ከሣሽ የሚያስረዳበትን መንገድ ይደነግጋል ፡፡ በመሆኑም በጊዜ ማለፍ ምክንያት ክሱ እንዲቋረጥ አያደርግም :: የይርጋ ሕግ በሌላ በኩል በጊዜ ማለፍ ምክንያት የመከሰስ መብት ስለሚያስቀር ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የማስረዳት ሸክም ወገን ማን ነው ? የማስረዳት ሸክሙን ተወጥቷል አልተወጣም ወዘተ .. ጥያቄዎችን በማንሳት ወደ ጉዳዩ ፍሬ ነገር ሊገባ አይችልም :: በመሆኑም የይርጋው ጊዜ በፍ.ብ.ሕ.ቁ .1845 መሠረት 1 ዐ ዓመት የሆነ ጉዳይ በዚሁ ህግ 2 ዐ 24 በተደነገገው የሕሊና ግምት መሠረት ሊስተናገድ ይችላል ፡፡ የይርጋ ጊዜው ያላለፈን ጉዳይ በሕጉ ቁጥር 2 ዐ 24 መሠረት እንደተከፈለ መቁጠር እርስ በርሱ የሚጋጭ ነገር ማከናወን አይደለም ::
አሁን በያዝነው ጉዳይ አመልካች ላቀረበው ክስ ምክንያት የሆነው የተመሠረተው በ 1981 መሆኑ ግራ ቀኙ ተስማምተውበታል ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሣሾች የሕጉ ግምት ተጠቃሚዎች ናቸው ያለው የተጠየቀው ክፍያ በ 1981 ዓ.ም መከፈል የነበረበት ነው በማለት ነው :: ለዚሁ መነሻ ያደረገው ተጨማሪ ፍሬ ነገር አመልካች ከ 1981 ዓ.ም ጀምሮ በዚሁ መከፈል ነበረበት በተባለው መጠን ላይ ወለድ መጠየቁ ነው :: አመልካች በሌላ በኩል ክፍያው መከፈል የነበረበት ገዜ ውሉ የተፈፀመበት 1981 ሳይሆን ጉዳዩ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች የሚታይ በመሆኑ ውሣኔ የተሰጠበት ጊዜ መሆን ነበረበት ብሏል ፡፡ ሆኖም ውሣኔ የተሰጠው መቼ እንደሆን ለሰበር አቤቱታ ባቀረበው ማመልከቻ ላይ አልገለፀም :: ሕጉ ከሚያዘው ከ 2 ዓመት በታች
መሆኑን ለማሣየት ክሱ ከቀረበበት ከ 1988 ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ በፊት የተወሰነ መሆኑን ማስረዳት ሲኖርበት በዚህ ረገድ የቀረበ ነገር የለም ፡፡ በመሆኑም ውሉ የተፈረመበትና በከሣሽ መከፈል ከነበረበት ተብሎ ለወለድ ስሌት መሠረት የሆነውን 1981 ዓ.ም መነሻ መደረጉ የሚነቀፍ አይደለም :: ክሱ በ 1988 ዓ.ም የቀረበ እንደመሆኑ ተከሣሾቹ የፍ.ብ.ሕ.ቁ .2024 ( ለ ) “ ለጠበቆች ፣ አዋዋዮች ለሌሎችም የሕግ አማካሪዎች በሙያ ሥራቸው ወይም በሹመት ሥራቸው ላደረጉት አገልግሎት የሚከፈል ዕዳ ዕዳው መከፈል ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚለው የህግ ግምት ተጠቃሚ ናቸው መባሉ በአግባቡ ነው ::
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሕግን ግምት ተፈጻሚ ከማድረግ አልፎ አመልካች ያቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዳል የሚል ውሣኔ ባለመሰጠቱ እንደአመልካች አባባል በፍ.ብ.ሕ.ቁ .1845 የሰፈረውን የይርጋ ህግ አለቦታው ተጠቅሞበታል ሊባል አይችልም :: በመሆኑም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን ክስ የፍ.ብ.ሕ.ቁ .2 ዐ 24 ( ለ ) ን መሠረት አድርጎ ውድቅ ማድረጉም ሆነ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ.ብ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ .337 ውድቅ ማድረጉ የህግ ስህተት መፈፀሙን የሚያመለክት አይደለም ፡፡
መልስ ሰጪዎች የሕግ ግምት ተጠቃሚ እስከሆኑ ድረስ ፣ የውሉ መኖሩን አለመካዳቸው ፣ በውሉ መሠረት ለመክፈል መስማማታቸውን ማመናቸው ፣ ውሉ ፈርሷል ብለው አለመከራከራቸወ ወዘተ … የሙግትን ውጤት የሚቀይረው አይደለም :: ውሉ አለ እንኳን ቢባል ዞሮ ዞሮ ክስ የቀረበበት የገንዘብ መጠን እንደተከፈለ መቆጠሩ የሚቀር አይደለም :: ይህ ሊቀር የሚችለው መሃላ እንዲወርድ ተጠይቆ እንደሆነና መሃላው የከሣሽን ክስ ያረጋገጠ እንደሆነ ነው :: ይህ ስለመሆኑ ከሰበር ማመልከቻውም ሆነ ከሥር ፍርድ ቤት መዝገብ የተገነዘብነው ነገር የለም ፡፡ በመሆኑም አመልካች ያቀረበው የሰበር ማመልከቻ የሕግ መሠረት የሌለው በመሆኑ አልተቀበልነውም ::
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ .5095 የካቲት 11 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ፀንቷል :: ይጻፍ ፡፡
You must login to view the entire document.