×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 22130

      Sorry, pritning is not allowed

S ልንበት የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ሰራተኛው በጡረታ ምክንያት ከስራ ትምህርት ቤት ውስጥ 4 , ሊያገለግሉ ከቆዩ በኋላ አመልካች መልስ ሰጭ
የካቲት 29 ቀን 1998 ዓ / ም
የመ / ቁ 22130 ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሠ
ዓብዱልቃድር መሐመድ ጌታቸው ምህረቱ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት መልስ ሰጭ፡- አቶ ግርማ መርሻ
ፍ ር ድ ጉዳይ የቀረበው የህግ ነጥብ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 የሚሰናበትበትን የህግ አግባብ የሚመለከት ነው ፡፡ በጉዳዩ መልስ ሰጭ በአመልካች
ዕድሜአቸው የጡረታ መውጫ የሆነው 60 አመት ላይ ደርሷል በሚል መልስ
ሰጭን ከስራ አሰናብቷል ፡፡ መልስ ሰጭ ስንብቱን በመቃወም ለፌዴራል የመጀመሪያ
ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ስንብቱ በአዋጅ ቁጥር
377/96 አንቀጽ 24 ( 3 ) መሰረት የተፈጸመ በመሆኑ ህጋዊ ነው በማለት የመልስ
ሰጭን ክስ ውድቅ አድርጎታል ፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ
ቤት በበኩሉ መልስ ሰጭ የጡረታ መውጫ እድሜ በሆነው 60 ዓመት ላይ
ደርሰዋል የተባለው በመንግሥት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ መሰረት በመሆኑና
አመልካችና መልስ ሰጭ ያደረጉት የስራ ውል የሚገዛው በአዋጅ ቁጥር 377/96
በመሆኑ ስንብቱን ለማድረግ የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት የለም በማለት የፌዴራል
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር አመልካች መልስ ሰጭን
የአንድ አመት ውዝፍ ደመወዝ ከፍሎ ወደ ስራ እንዲመልሳቸው በማለት ወስኗል ፡፡
አመልካች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ በመቃወም
ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው
ትእዛዝ መሰረት አመልካችና መልስ ሰጭ ክርክራቸውን ለችሎቱ በቃል አሰምተዋል ፡፡
ችሎቱም የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 ተፈጻሚ በሚሆንበት
የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ሰራተኛው በጡረታ ምክንያት ከስራ የሚሰናበትበትን የህግ
አግባብ መሰረት በማድረግ ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የስራ ውል በህጋዊ መንገድ
የሚቋረጥባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር ይደነግጋል ። በአዋጅ አንቀጽ 23 ( 1 ) መሰረት
እነዚህ ህጋዊ የስራ ማቋረጫ ምክንያቶች በአሰሪው አነሳሽነት ( አዋጁ በአንቀጽ 27 ፣
28 እና
መሠረት ) ወይም በሰራተኛው አነሳሽነት ( አዋጁ በአንቀጽ 31 እና 32
መሠረት ) !
በተደነገገው መሰረት ( በአዋጁ በአንቀጽ 24 መሰረት ) ወይም
በኀብረት ስምምነት መሰረት ወይም በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት መሰረት ( በአዋጁ
በአንቀጽ 25 መሰረት ) ናቸው ፡፡ አንድ የስራ ውል በህገ ወጥ መንገድ ተቋርጧል
የሚባለው የስራ ውሉ የተቋረጠው ከላይ ከተመለከቱት ምክንያቶች ውጭ እንደሆነ
ከላይ እንደተመለከተው የስራ ውል በህጋዊ መንገድ የሚቋረጥባቸውን
ምክንያቶች አንዱ በህግ በተደነገገው መሰረት በአዋጁ በአንቀጽ 24 መሰረት ነው ፡፡
የዚሁ ድንጋጌ ንዑስ አንቀጽ 3 ሰራተኛው አግባብ ባለው የጡረታ ህግ መሰረት
በጡረታ ሲገለል የስራ ውሉ በህግ መሰረት እንደሚቋረጥ ይደነግጋል ፡፡ ሆኖም
የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈጻሚ በሚሆንበት የስራ ውል ተፈጻሚ
የሚሆን የጡረታ ህግ የሌለ ሲሆን የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር
345/1995 ደግሞ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 ተፈጻሚ በሚሆንበት
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
( it ዕ / ግእ
በስራው ላይ እንዲቀጥል ' ' ላው አይደለም የሚለው ነው ፡፡ በዚህ ጉዳይም
ታሳቢ የተደረገው የጡረታ ህግና በመንግስት የስራ ውል ላይ ተፈጻሚ የሚሆን አይደለም ። በመሆኑም የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 24 ( 3 ) ሰራተኛው አግባብ ባለው የጡረታ ህግ መሰረት በጡረታ ሲገለል የስራ ውሉ በህግ መሰረት እንደሚቋረጥ የሚደነግገው ተፈጻሚ የሚሆነው እንዴት ነው የሚለውን መመርመር አስፈላጊ ይሆናል ፡፡
በመሰረቱ የትኛውም ሰራተኛ በጡረታ ምክንያት ከስራ እንዲሰናበት ሲደነግግ አንድ ሰራተኛ ዕድሜውን ሙሉ ብቃት ያለው ሰራተኛ ሆኖ እንደማይዘልቅና የሰው ልጅ ዕድሜ መግፋት በስራ ውጤታማነት ( የመስራት ችሎታ ) ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳለውና ሰራተኛው ዕድሜውን ሙሉ በተቀጠረበት ስራ ላይ እንዲቀጥል ቢደረግ የአሰሪው ( የድርጅቱ ) ጥቅም ያለአግባብ እንደሚጎዳ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሰራተኛው ከስራ ተሰናብቶ አሰሪው ብቃት ያለው ሰራተኛ በቦታው እንዲተካ ለማስቻልና ሰራተኛውም ከስራ ከተሰናበተ በኋላ ከጡረታ ስርዓት
መንገድ ለማመቻቸት ነው ። የጡረታ ህጎች የጋራ መነሻ መሰረታዊ
ከተወሰነ የጡረታ ዕድሜ ደረጃ በኋላ የሰራተኛው የስራ ብቃት በአዋጅ ቁጥር 377/96 24 ( 3 )
ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው የጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 ከላይ
የተመለከተውን ተመሳሳይ መሰረት ሃሳብ የሚጋሩ ናቸው ፡፡ በመሆኑም በአዋጅ
ቁጥር 377/96 24 ( 3 ) ታሳቢ የተደረገው የጡረታ ህግ ባለመውጣቱ ምክንያት
በድንጋጌው
አፈጻጸም ላይ
የሚያጋጥምን
የህግ ክፍተት ለመሙላት ከላይ
የተመለከተውን የጡረታ ህጎች የጋራ መነሻ መሰረት በማድረግ የጡረታ አዋጅ ቁጥር
345/1995 ድንጋጌዎችን መንፈስ ተጠቅሞ ክፍተቱን መሙላት የአዋጅ ቁጥር
377/96 24 ( 3 ) ድንጋጌን የተቃረነ ነው የሚባል አይደለም ፡፡
በዚህ ጉዳይ አመልካች መልስ ሰጭን ዕድሜአቸው የጡረታ መውጫ ዕድሜ
የሆነው 60 ዓመት ላይ ደርሰዋል በሚል ከስራ ያሰናበታቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
24 ( 3 ) ታሳቢ የተደረገው የጡረታ ህግ ባይወጣም በመንግስት ሰራተኞች ላይ
ተፈጻሚ የሚሆነው የጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 ድንጋጌዎችን መሰረት
በማድረግ ነው ፡፡ ከላይ እንደተመለከተው በአዋጅ ቁጥር 377/96 24 ( 3 ) ታሳቢ
የተደረገው የጡረታ ህግና በመንግስት ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው የጡረታ
አዋጅ ቁጥር 345/1995 ጡረታን የሚመለከቱ እንደመሆናቸው የሚጋሩትን የጡረታ
ህግ መሰረት መነሻ በማድረግ የአዋጅ ቁጥር 377/96 24 ( 3 ) ድንጋጌን ተፈጻሚ
ለማድረግ የጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/1995 ድንጋጌዎችን መንፈስ ተጠቅሞ
ክፍተቱን መሙላት የአዋጅ ቁጥር 377/96 24 ( 3 ) ድንጋጌን የተቃረነ ነው የሚባል
አይደለም ፡፡ በመሆኑም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጡረታ አዋጅ ቁጥር
345/1995 አንድ ሰራተኛ ዕድሜው 60 ዓመት ሲሞላው በጡረታ ከስራ
እንደሚሰናበት የተደነገገው ለመንግስት ሰራተኞች ነው በሚል ስንብቱ ህገ ወጥ ነው
ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል ።
ው ሣ ኔ
ይህ ችሎት
ሰጭ ከስራ የተሰናበተው በአግባቡ ነው በማለት
ወስኗል ፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ / ቁ 38757 ህዳር 13 ቀን 1998 ዓ / ም
የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል ፡፡
• አመልካችና መልስ ሰጭ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ
የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ነፃ ልንወ y

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?