የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፳፮ አዲስ አበባ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፳፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፴፰ / ፲፱፻፫፫ ዓ . ም - የማኅበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ገጽ ፻፲ አዋጅ ቁጥር ፴፰ ፲፱፻፳፰ የማኅበራዊ ዋስትና ባለሥልጣንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የማኅበራዊ ዋስትና ባለሥልጣንን ተግባሩን በብቃት በሚወ | ጣበት መልኩ ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፡ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | Security Authority in such a way as to enable it perform its መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። _ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የማኅበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ | 1 . Shor Title ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፳፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፩ . የማኅበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ( ከዚህ በኋላ “ ባለሥ ልጣኑ ” እየተባለ የሚጠራ ) የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ። _ የባለሥልጣኑ ተጠሪነት ለሚኒስትሮች ምክር ቤትይሆናል ። ነጋሪት ጋዜጣፖሣ . ቁ ተሺ ገጽ ፻፲፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም . Federal Negarit Gazeta - No . 26 2 July 1996 – Page191 ፫ : ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስ | ፈላጊነቱ በማናቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል ። የባለሥልጣኑ ዓላማ የማኅበራዊ ዋስትና ፕሮግራሞች እንዲ | ጠናከሩና እንዲስፋፉ ማድረግ ይሆናል ። ሥልጣንና ተግባር ባልሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ . የማኅበራዊ ዋስትና ሕጐች ፡ ደንቦችና መመሪያዎችን በሥራ ላይ ያውላል ፡ ፪ የማኅበራዊ ዋስትና ፕሮግራሞች ስለሚጠናከሩበትና ስለሚስፋፉበት ሁኔታ ጥናት እያካሄደ ለመንግሥት ያቀርባል ፡ ፫ . የማኅበራዊ ዋስትና መዋጮዎችን ይሰበስባል ፡ በየመ ሥሪያ ቤቱ የማኅበራዊ ዋስትና መዋጮ ሂሣብ መዝገብ በሚገባ መያዙን ያረጋግጣል ፡ አስፈላጊም ሲሆን ሰነዶችና መዛግብትን ይመረምራል ፡ መዋጮ በወቅቱ ገቢ በማያደርጉና መረጃዎችን በማይልኩ አሠሪ መሥሪያ ቤቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል ፣ የማኅበራዊ ዋስትና ፈንዶችን ያስተዳድራል ፡ ለእያን ዳንዱ ፈንድ የተለየ የሂሣብ መዝገብ ይይዛል ፤ ፭ ለማኅበራዊ ዋስትና መብት ብቁ የሚያደርጉ ማስረጃ ዎችን በቅድሚያ አሰባስቦ ያጣራል ፡ ይመዘግባል ፡ ከአሠሪ መሥሪያ ቤቶች በየጊዜው በሚደርሱት የለውጥ ማስታወቂያዎች መሠረት ማስረጃዎችን ወቅታዊ ያደርጋል ፡ • የማኅበራዊ ዋስትና ባለመብት አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ሊያገኝ የሚገባውን የአበል መጠን ይወስናል ፡ አስፈላጊ ሰነዶች መዘጋጀታቸውንና ክፍያ በአግባቡ መፈጸሙን ያረጋግጣል ፡ ፯ የአበል መክፈያ ጣቢያዎች ተለይተው እንዲታወቁ ያደርጋል ፡ አግባብ ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተ ባበር እንደአስፈላጊነቱ አዳዲስ የአበል መክፈያ ጣቢያ ዎችን ያቋቁማል ፡ ቿ አግባብ ባላቸው ሕጐች መሠረት በሚቀርቡ የማኅ _ በራዊ ዋስትና መብትና ጥቅም ጥያቄዎች ላይ ውሳኔ ይሰጣል ፤ ፬• ከማኅበራዊ ዋስትና መዋዎች ለክፍያና ለመጠባ በቂያ የሚውለውን ቀንሶ ቀሪውን ትርፋማና አስተ ማማኝ በሆኑ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ላይ ያውላል ፤ ፲ የማኅበራዊ ዋስትና ፈንዶች በየተወሰነ ጊዜ በሂሣብ ስሌት አዋቂዎች ( አክቹዋሪ ) እንዲጠኑናእንዲመረመሩ ያደርጋል ፤ የንብረት ባለቤት ይሆናል ' ውል ይዋዋላል ፣ በስሙ | ይከሳል ይከሰሳል ፡ ፲፪• ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባ | ሮችን ያከናውናል ። ፮ . የባለሥልጣኑ አቋም ባለሥልጣኑ ፡ ፩ . የሥራ አመራር ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ | 6 . Organization of the Authority የሚጠራ ) ፡ ገጽ የን ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፷ ዓ . ም . Federal Negarit Gazeta No . 26 2 July 1996 – Page 192 ፪• በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፡ እና ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ፡ ይኖሩታ ' ል ። ፯ - የቦርዱ አባላት ቦርዱ ሰብሳቢውን ጨምሮ በመንግሥት የሚሰየሙ አባላት ይኖሩታል ። ቁጥራቸውም እንደአስፈላጊነቱ ይወሰናል ። ፰ . የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተለት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፡ ፩ . የባለሥልጣኑን ሥራዎች በበላይነት ይመራል ፡ ይቆጣ | ፪ . የባለሥልጣኑን የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንዲሁም ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት መርምሮ ያጸድቃል ፡ - የማኅበራዊ ዋስትና ፈንዶችን አስተዳደር ይቆጣጠራል ፡ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ) መሠረት የሚደረጉ የኢንቨስት መንት ዕቅዶች መንግሥት በሚያወጣው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት መፈጸማቸውን ይቆጣጠራል ፡ 6 የባለሥልጣኑን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸድ ፭ : በዋናው ሥራ አስኪያጅ በሚቀርቡ የባለሥልጣኑን አስተዳ ደርና አመራር በሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይወስናል ። ሀ . የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ፡ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሰብሳቢው ጥሪ በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ። ፪ . በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተገኙ ምልዓተ | ጉባዔ ይሆናል ። • የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባሎች በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ነው ፡ ሆኖም ድምጹ እኩል ለእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። በ• ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፭ ለቦርዱ አባላት ሊከፈል የሚገባው አበል በመንግሥት ይወሰናል ። ፲ የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር ፩ . ዋናው ሥራ አስኪያጅ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ | 10 . Powers and Duties of the General Manager ሆኖ ቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሥራዎች ይመራል ፡ ያስተዳድራል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ዋናው ሥራ አስኪያጅ ፡ ሀ ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ የተመለከተውን የባለሥል ጣኑን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ ያውላል ፡ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማዎች ተከትሎ ቦርዱ በሚያጸድቀው መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፡ ያስተዳ ሐ ) የባለሥልጣኑን ዓመታዊ በጀትና የሥራ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፡ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፡ | ገጽ የን ! ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻ቸ፰ ዓም Federal Negarit Gazeta No . 26 _ 2 July 1996 Page 193 መ ) ለባለሥልጣኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፡ ሠ ) ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል : ረ ) የባለሥልጣኑን የሥራ እንቅስቃሴና የሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ። ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለባለሥልጣኑ ሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለባለሥ ልጣኑኃላፊዎችና ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስተ ላልፍ ይችላል ። ፲፩ ስለማኅበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ፩ . የማኅበራዊ ዋስትና መብትንና ጥቅምን በሚመለከት ባለሥልጣኑ በሚሰጠው ውሳኔ ላይ የሚቀርቡትን ይግባኞች እየመረመረ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥ የማኅ በራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ይቋቋማል ። ፪ . የጉባዔው አባላት አሰያየምና አደረጃጀቱ በመንግሥት መመሪያ ይወሰናል ። ፫ . የይግባኝ አቤቱታ ለጉባዔው መቅረብ የሚችለው ይግባኝ በሚባልበት ጉዳይ ላይ ውሳኔ በተሰጠ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ነው ። በ ገባዔው ይግባኝ የቀረበበትን የባለሥልጣኑን ውሳኔ መለወጥ ፡ ማሻሻል ወይም ማጽናት ይችላል ። ፭ ጉባዔው የራሱን የአሠራር ሥነ ሥርዓት ደንብ | 4 . The Tribunal may reverse , vary or confirm de ያወጣል ። ፲፪ በጀት የባለሥልጣኑ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ | ይሆናል ፡ ፩ . ባለሥልጣኑ ከሚያስገኛቸው የኢንቨስትመንትና ሌሎች ገቢዎች ፡ እና ፪• የፌዴራሉ መንግሥት ከሚሰጠው ድጐማ ። ፲፫ . ስለሂግብ መዛግብት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ | መዛግብት ይይዛል ። ፪ . የባለሥልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፬ . የተሻሩ ሕጐች የሚከተሉት በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ፡ ፩ . የመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ቁጥር ፪፻፱ ፲ሀየሃኑ ( እንደተሻሻለ ) ከአንቀጽ ፴፭ እስከ አንቀጽ ፵፩ ፡ ፪ . የመንግሥት አገልግሎት ጡረታ ጉባዔ ቻርተር የሕግ | ክፍል ማስታወቂያ ቁጥር ፪፻፶ ፲፱፻፶፬ ። መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ በሕግ ሳይቋቋም የጡረታና ማኅበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን | በመባል ይታወቅ የነበረው አካል መብትና ግዴታ በዚህ | አዋጅ ለባለሥልጣኑ ተላልፋል ። ገጽ ፻፲፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፮ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፰፰ ዓም . Federal Negarit Gazeta No . 26 2 July 1996 Page 194 አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻፰፰ ዓ . ም . ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፭ ቀን ፲፱፻T፰ ዓ•ም• ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ