የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት
የመ / ቁ .15835
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
አመልካች፡- ሼል ኢትዮጵያ አ / ማ
መልስ ሰጪ፡- ወ / ሮ አስቴር ብርሃነ ስላሴ
በከሳሽነት ወይም
የሙግት ተካፋይ ስለመሆን - ስለ ባለ ጉዳዩ ወደ ፍ / ቤት
ሳይቀርብ መቅረት
የተከሳሽ ያለመቅረብ - ጉዳዩ ለመልስ በተቀጠረ ዕለት የተከሳሽ
መልስ አለማቅረብ - የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥሮች 70፣233
የአሁኑ መልስ ሰጪ በከፍተኛው ፍ / ቤት በአመልካች ላይ በመሰረቱት ክስ
የአሁን አመልካችን መልስ ለመቀበል በተያዘው ቀጠሮ ቀርቦ መልስ ባለማቅረቡ ፍ / ቤቱ
ጉዳዩ በሌለበት እንዲታይ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ መ / ሰጭ ክሱን በማሻሻላቸው የተሻሻለው
ክስ እንደ አዲስ ክስ መቆጠር ስላለበት መልስ ልስጥበት በማለት አመልካች ያቀረበውን
ጥያቄ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ውድቅ ስላደረገውና ይህንኑ ትዕዛዝ
የፌዴራል
ጠቅላይ ፍ / ቤትም ስላጸናው የቀረበ አቤቱታ
ው ሳ ኔ፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ትዕዛዝ
ተሽሯል ፡፡
1- ተከሳሽን ከክሱ አስወጥቶ / ex parte / ጉዳዩ መታየቱ የሚቀጥለው ተከሳሹ ጉዳዩ
ሊሰማ በተቀጠረበት ቀን በችሎት ያልቀረበ እንደሆነ ነው ፡፡
2- ጉዳዩ የተከሳሽን መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን ተከሳሽ ያልቀረበ እንደሆነ
መልሱን በጽሁፍ ከማቅረብ ጋር ተያይዘው የሚነ
ጥቅሞች ይቀሩበታል እንጅ
በቀጣዩ ሂደት ከመሳተፍ አይከለከልም ፡፡
የጠቅላይ ፍ / ቤት የተቀበለወ
ሐምሌ 29 ቀን 1997 ዓ.ም
የመዝገብ ቁጥር 15835 ዳኞች አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ፍሥሐ ወርቅነህ
አብዱልቃድር መሐመድ ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
አቶ መሥፍን ዕዩበዮናስ አመልካች ሼል ኢትዮጵያ አክስዮን ማኀበር መልስ ሰጪ-- ወ / ሮ አስቴር ብርሃነ ስላሴ
በዚህ መዝገብ ለቀረበው ክርክር መነሻ የሆነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት የሰጠውና
ትዕዛዝ ነው :: የአሁኑ አመልካች ሁለቱም ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት የሰበር ማመልከቻ ያቀረቡ ሲሆን ጉዳዩ በሰበር መታየት ይገባዋል ተብሎ በመታዘዙ መልስ ሰጪም ቀርቦ በጉዳዩ
ላይ የጽሁፍ ክርክሩን አቅርቦአል ::
የአመልካች አቤቱታ ከፍተኛ ፍ / ቤት የከሣሽ ክስ እንዲሻሻል ትዕዛዝ መስጠቱን አውቆ ለተሻሻለው ክስ መልስ እንዲያቀርብ ሲጠይቅ ፍ / ቤቱ ቀደም ሲል በሥ.ሥ.ሕ.ቁ .73 መሠረት ጉዳዩ አመልካች በሌለበት እንዲታይ የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ የሥነ ሥርዓት ሕጉን የጣሰ አሠራር ነው በማለት በሰበር እንዲስተካከልለት አመልክቷል ፡፡ የአመልካች ዋና ክርክር የተሻሻለው ክስ እንደ አዲስ ክስ መቆጠር ስላለበት ቀደም ብሎ ክርክሩ በሌለበት እንዲታይ የተወሰነ ቢሆንም ለተሻሻለው ክስ መልስ የመስጠት መብቱ ሊቀርበት አይገባም የሚል ነው :: መልስ ሰጪ በዚህ ጉዳይ ላይ መልሱን በጽሁፍ በማቅረብ የክሱ መሻሻል ቀደም ሲል የተሰጡትን ትዕዛዞች የሚሽር ባለመሆኑ አመልካች ለተሻሻለው ክስ መልስ ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ በሁለቱም ፍ / ቤቶች የሕግ ስህተት መኖሩን አያሳይም በማለት ተከራክሯል ፡፡
ይህ የሰበር ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ አመልካች መልስ ለማቅረብ በተቀጠረበት ቀን መልሱን ይዞ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በሌለበት እንዲታይ መታዘዙን ተገንዝቧል ፣ በተሻሻለው ክስ መልስ ሊያቀርብ አይገባም የሚል ትዕዛዝ የተሰጠውም ቀደም ብሎ የተሰጠውን
ትዕዛዝ መሠረት በማድረግ እንደሆነ ተረድቷል ፡፡ በዚህም መሠረት ጉዳዩን በአግባቡ ለማስተናገድ የአሁኑ አመልካች መልስ እንዲያቀርብ በተቀጠረበት ዕለት መልሱን ይዞ ባለመቅረቡ የሚከተለው ህጋዊ ውጤት ምንድነው ? የሚለውንና ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ነጥቦች መመርመር ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል ፡፡
አንድ ተከሣሽ ጉዳዩ ለመልስ በተቀጠረበት ዕለት መልሱን ይዞ ካልቀረበ ክርክሩ በሌለበት የሚሰማ መሆኑ ፍርድ ቤቱ በሚልክለት መጥሪያ ላይ እንደሚገለጽለት በፍሥ.ሥ.ሕ.ቁ. 233 ላይ ተደንግጓል :: በሌላ በኩል የፍ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ .7 ዐክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሣሽ ቀርቦ ተከሣሽ ያልቀረበ እንደሆነ ተከሣሹ ያልቀረበው የተላከለት መጥሪያ ደርሶት ከሆነ ተከሣሹ በሌለበት የነገሩ መሰማት እንደሚቀጥል ይደነግጋል ፡፡ እነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች ሁለት በተለያየ ጊዜ የሚከናወነ የሙግት ደረጃዎችን የሚመለከቱ ቢሆንም የተከሣሽን መቅረት አስመልክቶ የሚያስከትሉት ውጤት ተመሳሳይ ይመስላል ፡፡ የጽሁፍ መልሱን ሳያቀርብ የቀረ ተከሣሽ በ 233 መሠረት በሌለበት ጉዳዩ እንደሚሰማ ፣ ጉዳዩ ለመሰማት በተቀጠረበት ቀን ያልቀረበ ተከሣሽም በተመሳሳይ ሁኔታ ጉዳዩ በሌለበት እንደሚስማ በቁጥር 70 ( ሀ ) መሠረት ትዕዛዝ የሚሰጥበት ይመስላል ፡፡ የሁለቱም ድንጋጌዎች የአማርኛ ቅጂ ለመልስ በተቀጠረበት ቀን መቅረትና ጉዳዩ እንዲሰማ በተቀጠረበት ቀን መቅረት አንድ ዓይነት ውጤት ያላቸው እንደሆነ የሚገልጹ ቢሆንም የሁለቱም የእንግሊዝኛ ቅጂዎች ግን የተለየ ጽንሰ ሃሣብ የሚያስተላልፉ ናቸው :: የእግንሊዝኛ የ 7 ዐወ ) ድንጋጌ ስለ Ex - parte ሲናገር የ 233 ግን የሚደነግገው ስለ default proceeding ነው :: ሁለቱም የተለያየ ይዘት የተለያየ ውጤት ያላቸው ናቸው ፡፡ የ 7 ዐ ( ሀ ) የእንግሊዝኛ ቅጂ
በማለት ሲደነግግ አግባብነት ያለው የ 233 ክፍል ደግሞ
በማለት ይደነግጋል ፡፡
ሁለቱንም የእንግሊዝኛ ቅጂዎች በማነጻጸር ለመገንዘብ እንደሚቻለው ለመልስ በተቀጠረ ቀን ተከሣሽ መልሱን ይዞ ባይቀርብ የሚከተለው ውጤት ለመሰማት በተቀጠረበት ቀን
$ ካሣሽ ከክስ እንዲወጣ መደረግ ያለበት ጉዳዩ እንዲሰማ ባይገኝ ከሚከተለው ውጤት ጋር አንድ ዓይነት አይደለም :: የ 233 ድንጋጌ መልሱን ባያቀርብም የጉዳዩ መሰማት እንደሚቀጥል ( default proceeding ) ከሚያሳይ በቀር ተከሣሽ ከክርክር እንዲወጣ የሚደረግበት ሥርዓት አለመኖሩ ያሳያል :: በ 70 ( ሀ ) ያለው ድንጋጌ በሌላ በኩል ጉዳዩ ለመሰማት በተቀጠረበት ቀን የቀረ ተከሣሽ ጉዳዩ እሱ በሌለበት መቀጠል ( default proceeding ) ብቻ ሳይሆን ከክርክሩ እንዲወጣ ( ex - parte ) እንደሚደረግ ያስቀምጣል ::
በአማርኛው ቅጂ ያለው አገላለጽ በእንግሊዝኛው ያለውን ሃሣብ በትክክል አለማስተላለፉን ያመለክታል ፡፡ የትርጉም ልዩነት ሲኖር የአማርኛውን ቅጂ በመውሰድ ዕልባት መስጠት ይቻላል በማለት ጉዳዩን ማጠቃለል አንዱ አማራጭ ነው :: ሆኖም ይህ አማራጭ አሁን በያዝነው ጉዳይ በግልጽ የሚታየውን የትርጉም ስህተት እንዲቀጥል የሚያደርግ በመሆኑ ትክክለኛ አማራጭ ነው አንልም :: ይልቁንም የተከሰተውን የትርጉም ልዩነት ከአጠቃላይ የሕጉ ዓላማ እንዲሁም ተከሣሽ በቀረበበት ክስ የመደመጥ መብትን ይበልጥ ሊያስከብር በሚችል ሁኔታ መተርጎም በበለጠ የፍትህ አስተዳደርን ዓላማ ስለሚያሳካ የእንግሊዝኛ ው ቅጂ መከተሉን መርጠናል ፡፡ በዚህም መሠረት አንድ በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ እንደሆነ እንጂ መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት ዕለት መሆን የለበትም :: ይህ አተረጓጎም ተከሣሹ መልስ ለመቀበል በተያዘ ቀጠሮ ሳይቀርብ ቢቀር ፍርድ ቤቱ ምን ያደርጋል የሚል ጥያቄ ማስከተሉ የሚቀር አይደለም :: ይህን ጥያቄ ለመመለስ ፍርድ ቤት የሰጠው ቀጠሮ ሳይከበር ቢቀር ፍርድ ቤቱ ምን ያደርጋል ከሚል ሌላ ጥያቄ ጋር ተያይዞ መመለስ ያለበት ነው ::
በሙግት ሂደት ፍርድ ቤት የተለያዩ ጉዳዮች መከናወናቸውን ለማረጋገጥ የተለያዩ ቀጠሮዎችን ይሰጣል :: ሆኖም ፍርድ ቤቱ የሰጠው ቀጠሮ በአንዱ ወይም በሌላው ተሟጋች በተስተጓጎለ ቁጥር ለመስተጓጎሉ ምክንያት የሆነው ወገን ከክርክር እንዲወጣ ( Exparte ) አይደረግም ፡፡ የቀጠሮው አለመከበር ቀጠሮው ከተሰጠበት ምክንያት ተነጥሎ የሚታይ ባለመሆኑ በየጉዳዩ የተለያየ ትዕዛዝ የሚሰጥ ቢሆንም መሠረታዊ የጉዳዩ ሂደት የሚስተናገደው በሥነ ሥርዓት ሕግ ምዕራፍ 7 በሚገኙት መርሆዎችና ድንጋጌዎች መሠረት መሆን አለበት :: በፍሥሥሕቁ .194 እንደተገለፀው በተወሰነ ጊዜ ገደብ ውስጥ መከናወን ያለበት ድርጊት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ካልተከናወነ ዋጋ እንደሌለው ይገልጻል፡፡በዚህም መሠረት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ መልሱን እንዲያቀርብ የታዘዘ ተከሣሽ መልሱን ባለማቅረቡ ይኸው ድርጊት ባለመፈፀሙ መልሱን በጽሁፍ ከማቅረብ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥቅሞች ይቀሩበታል :: በቀጣዩ ሂደት ከመሳተፍ ግን አይከለከልም ::
° ከፍተኛ ፍ / ቤት በሚደረገው ክርክር ከክርክር ውጪ ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ የአሁን አመልካች በተሻሻለው ክስ ላይ መልስ መስጠት አትችልም የተባለው ቀደም ብሎ ጉዳዩ መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን መልሱን ይዞ አለመቅረቡን ምክንያት በማድረግ ነው :: ሆኖም ጉዳዩ ለመልስ በተቀጠረ ቀን ተከሣሹ መልሱን ሳያቀርብ ቢቀር የጽሁፍ መልስና የማስረጃ ዝርዝር የማቅረብ ዕድሉን ከሚያጣ በቀር ከክርክሩ ውጪ እንዲሆን መታዘዝ አልነበረበትም :: በዚህም ምክንያት አንድን ተከሣሽ ህጉ ከሚፈቅደው ሁኔታ ውጪ ከክርክር ውጪ ማድረግ በጉዳዩ ላይ የሥነ ሥርዓት ግድፈት መፈፀሙን ያመለክታል ፡፡ ክሱ እንዲሻሻል ትዕዛዝ ሲሰጥ ተከሣሹ መልስ ማቅረብ አትችልም የተባለው ከዚህ የሥነ ሥርዓት ግድፈት በተያያዘ ምክንያት ነው ፡፡ አመልካቹ ከክርክሩ መውጣት ሳይኖርበት አውጥቶ ለተሻሻለው ክስ መልስ አታቀርብም መባሉ አግባብ አይደለም :: የጠቅላይ ፍ / ቤት የሥነ ሥርዓት ግድፈት መፈፀሙን በማመን ይህን ግድፈት ማስተካከል ሲገባው አልፎታል ፡፡ በመሆኑም የሰበር የተፈፀመውን በፍ.ሥ.ሥ.ሕግ በተደነገገው መሠረት ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል ::
1. የአሁኑ አመልካች
የተደረገው በአግባቡ ስላልሆነ ወደ ክርክሩ ይግባ :: 2. ለተሻሻለው ክስ መልስ ማቅረብ እንዲችል ከፍተኛው ፍ /
ቤት የተሻሻለውን ክስ ግልባጭ ይሰጠው :: 3. ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ::
You must login to view the entire document.